Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 32:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እን​ዳ​ላ​ሸ​ነ​ፈ​ውም ባየ ጊዜ የጭ​ኑን ሹልዳ ያዘው፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጭኑ ሹልዳ ሲታ​ገ​ለው ደነ​ዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ በግብግቡም የያዕቆብ ጭን ከመጋጠሚያው ላይ ተናጋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ያ ሰው ያዕቆብን እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ፥ የጭኑን ሹልዳ ነካው፥ ያዕቆብም ሲታገለው የጭኑ ሹልዳ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ያ ሰው ያዕቆብን በትግል ማሸነፍ እንዳቃተው ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ መታው፤ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 32:25
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ግ​ዲህ ፍጠ​ንና በዚያ ራስ​ህን አድን፤ ወደ​ዚያ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ድረስ ምንም አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ል​ምና።” ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።


ያዕ​ቆብ ግን ለብ​ቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታ​ገ​ለው ነበር።


እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወ​ር​ችን ሹልዳ አይ​በ​ሉም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ጭን ይዞ የወ​ር​ቹን ሹልዳ አደ​ን​ዝ​ዞ​አ​ልና።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም የፈ​ጠረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦ ስለ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች ጠይ​ቁኝ፤ ስለ እጄም ሥራ እዘ​ዙኝ።


ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፤ መንፈስስ ተዘጋጅታለች፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፤” አለው።


ደግሞም ትቶአቸው ሄደ፤ ሦስተኛም ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች