Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 32:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ስለዚህ እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ፥ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት እዚያው በሰፈሩበት አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በዚህ ዐይነት ስጦታውን አስቀድሞ ከላከ በኋላ፥ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት በሰፈር አደረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 32:21
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።”


በዚ​ያ​ችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለ​ቱን ሚስ​ቶ​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ዕቁ​ባ​ቶ​ቹን ዐሥራ አን​ዱ​ንም ልጆ​ቹን ይዞ የያ​ቦ​ቅን ወንዝ ተሻ​ገረ።


ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።


አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።


ትምህርት ገንዘብ ለሚያደርጓት የባለሟልነት ዋጋ ናት፥ ወደ ተመለሰችበትም መንገድን ታቀናለታለች።


ኢያ​ሱም ላካ​ቸው፤ ወደ​ሚ​ደ​በ​ቁ​በ​ትም ስፍራ ሄዱ፤ በጋ​ይና በቤ​ቴል መካ​ከ​ልም በጋይ በባ​ሕር በኩል ተቀ​መጡ፤ ኢያሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሕ​ዝቡ መካ​ከል አደረ።


ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ዋም፥ “አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ በፊቴ ሂዱ፤ እነ​ሆም እከ​ተ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አለች። ይህ​ንም ለባ​ልዋ ለና​ባል አል​ነ​ገ​ረ​ች​ውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች