Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

65 ሎሌ​ው​ንም፥ “ሊቀ​በ​ለን በሜዳ የሚ​መጣ ይህ ሰው ማነው?” አለ​ችው። ሎሌ​ውም፥ “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት፤ እር​ስ​ዋም ቀጸ​ላ​ዋን ወስዳ ተከ​ና​ነ​በች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

65 አገልጋዩንም፣ “ይህ ሊገናኘን በመስኩ ውስጥ ወደዚህ የሚመጣው ሰው ማን ነው?” ስትል ጠየቀችው። አገልጋዩም፣ “ጌታዬ ነው” ብሎ መለሰላት፤ እርሷም መሸፈኛዋን ተከናነበች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

65 ሎሌውንም፦ “ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው?” አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

65 “ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?” ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም “እርሱ ጌታዬ ነው” አላት። ስለዚህ በፍጥነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

65 ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:65
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሣራ​ንም አላት “እነሆ፥ ለወ​ን​ድ​ምሽ አንድ ሺህ ምዝ​ምዝ ብር ሰጠ​ሁት፤ ይህም ለፊ​ትሽ ክብር ይሁ​ንሽ፤ በሁ​ሉም እው​ነ​ትን ተና​ገ​ራት።”


ርብ​ቃም ዓይ​ኖ​ች​ዋን አቀ​ናች፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም አየች፤ ከግ​መ​ልም ወረ​ደች።


ሎሌ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን ነገር ሁሉ ለይ​ስ​ሐቅ ነገ​ረው።


እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና።


መስ​ተ​ዋ​ቱ​ንም ከጥሩ በፍታ የተ​ሠ​ራ​ው​ንም ልብስ፥ ራስ ማሰ​ሪ​ያ​ው​ንም፥ ዐይነ ርግ​ቡ​ንም ያስ​ወ​ግ​ዳል።


ወፍጮ ወስ​ደሽ ዱቄ​ትን ፍጪ፤ ክን​ብ​ን​ብ​ሽን ግለጪ፤ ሽበ​ትሽ ይታይ፤ ባት​ሽን ግለጪ፤ ወን​ዙ​ንም ተሻ​ገሪ።


ስለ​ዚ​ህም ሴት ስለ መላ​እ​ክት፥ ሥል​ጣን ለራ​ስዋ ሊሆን ይገ​ባል፤


እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች