Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 እኅ​ታ​ቸው ርብ​ቃ​ንም መረ​ቁ​አ​ትና፥ “አንቺ እኅ​ታ​ችን፥ እልፍ አእ​ላ​ፋት ሁኚ፤ ዘር​ሽም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይው​ረስ” አሉ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ርብቃንም እንዲህ ብለው መረቋት፤ “እኅታችን ሆይ፤ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽ የጠላቶቹን ደጆች ይውረስ”።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 ርብቃንም መረቁአትና፦ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፥ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ” አሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 “አንቺ እኅታችን የብዙ ሺህ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዘሮችሽም የጠላቶቻቸውን ከተሞች ይውረሱ!” ብለው ርብቃን መረቁአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ርብቃንም መረቁአትና፦ አንቺ እኅታችን እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ አሉአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:60
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም፤ የባ​ሕ​ርን ዓሣ​ዎ​ች​ንና የም​ድር አራ​ዊ​ትን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና እን​ስ​ሳ​ት​ንም ሁሉ፥ በም​ድር ላይ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ግዙ​አ​ቸው።”


አብ​ራ​ም​ንም ባረ​ከው፤ “አብ​ራም ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ለፈ​ጠረ ለል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ባ​ረከ ነው፤


እባ​ር​ካ​ታ​ለ​ሁና፥ ከአ​ን​ተም ልጆ​ችን እሰ​ጣ​ታ​ለ​ሁና፤ አሕ​ዛ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ከእ​ር​ስዋ ይወ​ጣሉ።”


ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብ​ትና በባ​ሕር ዳር እን​ዳለ አሸዋ ፈጽሞ አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ዘር​ህም የጠ​ላት ሀገ​ሮ​ችን ይወ​ር​ሳሉ፤


ርብ​ቃም ተነ​ሣች፤ ደን​ገ​ጥ​ሮ​ች​ዋም፥ በግ​መ​ሎ​ችዋ ላይ ተቀ​ም​ጠው ከሰ​ው​ዬው ጋር አብ​ረው ሄዱ፤ ሎሌ​ውም ርብ​ቃን ተቀ​ብሎ ሄደ።


አም​ላኬ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ፤ ከፍ ከፍም ያድ​ር​ግህ፤ ይባ​ር​ክህ፤ ያብ​ዛህ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ሁን ፤


ያዕ​ቆ​ብም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ በዐ​ይ​ኖ​ቹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሠራ​ዊት ከት​መው አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክ​ትም ተገ​ና​ኙት።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “በእ​ና​ንተ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ተብሎ ይባ​ረ​ካል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኤፍ​ሬ​ምና እንደ ምናሴ ይባ​ር​ክህ።” ኤፍ​ሬ​ም​ንም ከም​ናሴ ፊት አደ​ረ​ገው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅ​ንና ልጆ​ቹን ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድ​ር​ንም ሙሉ​አት፤ ግዙ​አ​ትም።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አጋቡ፤ እነ​ር​ሱም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ይው​ለዱ፤ ከዚ​ያም ተባዙ፤ ጥቂ​ቶ​ችም አት​ሁኑ።


ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ታወ​ር​ሱ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ና​ንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ውርስ ይሆ​ናሉ፤ ነገር ግን ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማና​ቸ​ውም ሰው ወን​ድ​ሙን በሥራ አያ​ስ​ጨ​ን​ቀው።


አባ​ቱና እናቱ ይዘው ወደ ከተ​ማዉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ​ሚ​ኖ​ር​በ​ትም ስፍራ በር ይው​ሰ​ዱት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች