Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ያም ሰው ሊገ​ና​ኛት ሮጠና፥ “ከእ​ን​ስ​ራሽ ጥቂት ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 አገልጋዩም ወደ እርሷ ፈጥኖ ቀረበና፣ “እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ሎሌውም ሊያናግራት ሮጠና፦ “ከእንስራሽ ጥቂት ውኃ ታጠጪኝ ዘንድ እለምንሻለሁ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አገልጋዩም ወደ እርስዋ ሮጦ ሄደና “እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ሎሌውም ሊገናኛት ሮጠና፦ ከእንስራሽ ጥቂት ውኃ ታጠጪኝ ዘንድ እለምንሻለሁ አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:17
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም በልቤ ያሰ​ብ​ሁ​ትን ሳል​ፈ​ጽም እን​ዲህ ሆነ፤ ያን ጊዜ ርብቃ እን​ስ​ራ​ዋን በት​ከ​ሻዋ ተሸ​ክማ ወጣች፥ ወደ ምን​ጭም ወርዳ ውኃ ቀዳች፤ እኔም “እስቲ ውኃ አጠ​ጪኝ” አል​ኋት።


ተነ​ሥ​ቶም ወደ ሰራ​ፕታ ሄደ፤ ወደ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በር በደ​ረሰ ጊዜ አን​ዲት መበ​ለት በዚያ እን​ጨት ትለ​ቅም ነበር፤ ኤል​ያ​ስም ጠርቶ፥ “የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመ​ጭ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሻ​ለሁ” አላት።


በቴ​ማን የም​ት​ኖሩ ሆይ፥ ወደ ተጠ​ሙት ሰዎች ውኃ አምጡ፤


በታ​ላ​ቅም እል​ቂት ቀን ግን​ቦች በወ​ደቁ ጊዜ፥ በረ​ዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ወን​ዞ​ችና የውኃ ፈሳ​ሾች ይሆ​ናሉ።


የሚ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም ያጽ​ና​ና​ቸ​ዋ​ልና፥ በውኃ ምን​ጮ​ችም በኩል ይመ​ራ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙም፤ የፀ​ሐይ ትኩ​ሳ​ትም አይ​ጐ​ዳ​ቸ​ውም።


እነሆ፥ ከሰ​ማ​ርያ አን​ዲት ሴት ውኃ ልት​ቀዳ መጣች፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ውኃ አጠ​ጪኝ” አላት።


ያቺ የሰ​ማ​ርያ ሴትም፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን፥ እኔም ሳም​ራ​ዊት ስሆን እን​ዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልት​ጠጣ ትለ​ም​ና​ለህ?” አለ​ችው፤ አይ​ሁድ ከሳ​ም​ራ​ው​ያን ጋር በሥ​ር​ዐት አይ​ተ​ባ​በ​ሩም ነበ​ርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች