Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 23:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እር​ሻ​ውና በእ​ርሱ ያለው ዋሻም በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአ​ብ​ር​ሃም የመ​ቃ​ብር ርስት ሆኖ ጸና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ዕርሻውና ውስጡ የሚገኘው ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያውያን ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በሒታውያን ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ የሒታውያን የነበረው እርሻ በውስጡ ካለው ዋሻ ጋር የአብርሃም የመቃብር ርስት ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እርሻውና በእርሱ ያለው ዋሻው በኬጢ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 23:20
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከነ​ዓ​ንም የበ​ኵር ልጁን ሲዶ​ንን፥ ኬጤ​ዎ​ንን፥


ከዚ​ህም በኋላ አብ​ር​ሃም ኬብ​ሮን በም​ት​ባል በመ​ምሬ ፊት በከ​ነ​ዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ሚስ​ቱን ሣራን ቀበረ።


“እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ ስደ​ተ​ኛና መጻ​ተኛ ነኝ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ እን​ድ​ገዛ የመ​ቃ​ብር ርስት ስጡኝ፤ ሬሳ​ዬ​ንም እንደ እና​ንተ ልቅ​በር።”


ይህም አብ​ር​ሃም ከኬጢ ልጆች የገ​ዛው እርሻ ነው፤ አብ​ር​ሃ​ም​ንና ሚስ​ቱን ሣራን በዚያ ቀበ​ሩ​አ​ቸው።


ልጆቹ ይስ​ሐ​ቅና ይስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ምሬ ፊት ለፊት ባለው በኬ​ጢ​ያ​ዊው በሰ​ዓር ልጅ በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ቀበ​ሩት።


እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እኔ ወደ ወገ​ኖች እሰ​በ​ሰ​ባ​ለሁ፤ በኬ​ጢ​ያ​ዊው በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ​ችው ዋሻ ከአ​ባ​ቶች ጋር ቅበ​ሩኝ፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር በመ​ምሬ ፊት ያለች፥


ልጆ​ቹም ወደ ከነ​ዓን ምድር መለ​ሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆ​ነች ዋሻም ቀበ​ሩት፤ እር​ስ​ዋም በመ​ምሬ ፊት ያለች፥ አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት ዋሻ ናት።


አባቴ ሳይ​ሞት አም​ሎ​ኛል፤ እን​ዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ በቈ​ፈ​ር​ሁት መቃ​ብር በከ​ነ​ዓን ምድር በዚያ ቅበ​ረኝ።’ አሁ​ንም ወጥቼ አባ​ቴን ልቅ​በ​ርና ልመ​ለስ።”


ንጉ​ሡም ኦር​ናን፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በዋጋ ከአ​ንተ እገ​ዛ​ለሁ፤ ለአ​ም​ላ​ኬም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያለ ዋጋ አላ​ቀ​ር​ብም” አለው። ዳዊ​ትም አው​ድ​ማ​ው​ንና በሬ​ዎ​ቹን በአ​ምሳ ሰቅል ብር ገዛ።


ምና​ሴም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በቤ​ቱም አጠ​ገብ ባለው በዖዛ አት​ክ​ልት ቦታ ተቀ​በረ፤ ልጁም አሞጽ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች