Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 18:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አብ​ር​ሃ​ምም እን​ደ​ገና ነገ​ሩን ደገመ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገ​ኙሳ?” እር​ሱም፥ “ስለ ሠላ​ሳው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ደግሞም አብርሃም፣ “ጌታዬ አይቈጣ፤ እባክህ ልናገር፤ ሠላሳ ጻድቃን ብቻ ቢገኙስ?” እርሱም፣ “ሠላሳ ባገኝ አላጠፋትም” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 እርሱም፦ “ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ከዚያ ሰላሳ ባገኝ አላጠፋም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ እባክህ አትቈጣ፤ እንደገና ልናገር፤ ምናልባት ሠላሳ ብቻ ቢገኙስ?” አለ። እግዚአብሔርም “ሠላሳ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 18:30
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ር​ሃ​ምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገ​ኙሳ?” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ለአ​ር​ባው ስል አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።


ደግ​ሞም፥ “እነሆ፥ ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እነ​ጋ​ገር ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ካገ​ኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገ​ኙሳ?” አለው። እር​ሱም፥ “ስለ ሃያው አላ​ጠ​ፋ​ትም” አለው።


ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።


“አንተ ስታ​ስ​ተ​ም​ረኝ እኔ የም​መ​ል​ሰው ምን አለኝ? ይህ​ንስ እየ​ሰ​ማሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እከ​ራ​ከር ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማ​ኖር በቀር የም​መ​ል​ሰው ምን​ድን ነው?


እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።


ደማ​ቸ​ውን የሚ​መ​ራ​መር እርሱ አስ​ቦ​አ​ልና፥ የድ​ሆ​ች​ንም ጩኸት አል​ረ​ሳ​ምና።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


ጌዴ​ዎ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “በቍ​ጣህ አት​ቈ​ጣኝ፤ ደግሞ አን​ዲት ነገር ልና​ገር፤ ጠጕሩ ብቻ​ውን ደረቅ ይሁን፤ በም​ድ​ሩም ላይ ጠል ይው​ረድ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች