Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “በሰ​ዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድ​ቃን ባገኝ ከተ​ማ​ውን ሁሉ ስለ እነ​ርሱ አድ​ና​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እግዚአብሔርም፣ “በሰዶም ከተማ ዐምሳ ጻድቃን ባገኝ ለእነርሱ ስል አገሪቱን በሞላ እምራለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እግዚአብሔርም፦ “በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እግዚአብሔርም “በሰዶም ከተማ ውስጥ በደል ያልሠሩ ኀምሳ ደጋግ ሰዎች ባገኝ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን ፈጽሞ አላጠፋም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እግዚአብሔርም፤ በሰዶም በከተማይቱ ውስጥ አምስ ጻድቃን ባገኝ ስፍራውን ሁሉ ስለ እነርሱ እምራለሁ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 18:26
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እኔ የማ​ደ​ር​ገ​ውን ከወ​ዳጄ አብ​ር​ሃም አል​ሰ​ው​ርም፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን የቀ​ሩት ይድ​ናሉ።


በዚ​ያም ወራት እስ​ራ​ኤል ለግ​ብ​ፅና ለአ​ሦር ሦስ​ተኛ ይሆ​ናል፤ በም​ድ​ርም መካ​ከል በረ​ከት ይሆ​ናል።


በእ​ር​ስ​ዋም ዘንድ ዐሥ​ረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃ​ጠ​ላል፤ ቅጠ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም በረ​ገፉ ጊዜ እንደ ግራ​ርና እንደ ኮም​በል ዛፍ ሁነው ይቀ​ራሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የወ​ይን ፍሬ በዘ​ለ​ላው በተ​ገ​ኘች ጊዜ፦ በረ​ከት በእ​ር​ስዋ ላይ አለና አታ​ጥ​ፉት እን​ደ​ሚ​ባ​ለው፥ ሁሉን እን​ዳ​ላ​ጠፋ ስለ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዲህ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


“በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መን​ገ​ዶች ሩጡ፤ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ ዕወ​ቁም፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይ​ዋም ፈልጉ፤ ፍር​ድን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን እው​ነ​ት​ንም የሚ​ሻ​ውን ሰው ታገኙ እንደ ሆነ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ቅጥ​ርን የሚ​ጠ​ግ​ንን፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋት በፈ​ረ​ሰ​በት በኩል በፊቴ የሚ​ቆ​ም​ላ​ትን ሰው ከእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ፈለ​ግሁ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘ​ሁም።


እነዚያ ቀኖችስ ባያጥሩ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነም ነበር፤ ነገር ግን እነዚያ ቀኖች ስለ ተመረጡት ሰዎች ያጥራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች