Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 5:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ይህም ምሥ​ጢር ታላቅ ነው፤ እኔም ይህ​ንኑ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስና ስለ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያኑ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ይህ ጥልቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እናገራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እናገራለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ ይህንንም የምለው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 5:32
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


ሙሽራ ያለ​ችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚ​ሰ​ማው የሙ​ሽ​ራው ሚዜ ግን በሙ​ሽ​ራው ቃል እጅግ ደስ ይለ​ዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈ​ጸ​መች።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ ቅን​ዐት እቀ​ና​ላ​ች​ኋ​ለ​ሁና፤ ወደ እርሱ አቀ​ር​ባ​ችሁ ዘንድ ለአ​ንዱ ንጹሕ ድን​ግል ሙሽራ ለክ​ር​ስ​ቶስ አጭ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


“ስለ​ዚ​ህም ወንድ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ከሚ​ስ​ቱም ጋር አንድ ይሆ​ናል፤ ሁለ​ቱም አንድ አካል ይሆ​ናሉ።”


እን​ግ​ዲ​ያስ እና​ን​ተም ሁላ​ችሁ እን​ዲሁ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁን እንደ ራሳ​ችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባል​ዋን ትፍ​ራው።


ለእ​ኔም፦ ቃልን እን​ዲ​ሰ​ጠኝ፥ አፌ​ንም ከፍቼ የወ​ን​ጌ​ልን ምሥ​ጢር በግ​ልጥ እን​ድ​ና​ገር ጸል​ዩ​ልኝ።


ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው።


እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


እንዲሁም ዲያቆናት ጭምቶች፥ በሁለት ቃል የማይናገሩ፥ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጎመጁ፥ ለነውረኛ ረብ የማይስገበገቡ፥


ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች