Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እና​ንተ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ልት​ሆኑ በእ​ርሱ ታነ​ጻ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እናንተም ደግሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ ዐብራችሁ እየተገነባችሁ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚያድርበት ሕንጻ ለመሆን እናንተም አብራችሁ በክርስቶስ ትታነጻላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 2:22
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆና​ችሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ስም በእ​ና​ንተ ላይ አድሮ እን​ደ​ሚ​ኖር አታ​ው​ቁ​ምን?


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ እን​ተ​ባ​በ​ራ​ለ​ንና፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋ​ዮች ነንና፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕንፃ ናችሁ።


ሥጋ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለተ​ቀ​በ​ላ​ች​ሁት በእ​ና​ንተ አድሮ ላለ ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ ቤተ መቅ​ደስ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? ለራ​ሳ​ች​ሁም አይ​ደ​ላ​ች​ሁም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”


በል​ባ​ችሁ ውስጥ በፍ​ቅር ሥር መሠ​ረ​ታ​ችሁ የጸና ሲሆን ክር​ስ​ቶስ በሃ​ይ​ማ​ኖት በሰው ውስጥ ያድ​ራ​ልና።


ትእዛዙንም የሚጠብቅ በእርሱ ይኖራል እርሱም ይኖርበታል፤ በዚህም በእኛ እንዲኖር ከሰጠን ከመንፈሱ እናውቃለን።


ከመንፈሱ ስለ ሰጠን፥ በእርሱ እንድንኖር እሱም በእኛ እንዲኖር በዚህ እናውቃለን።


እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች