Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 በነ​ቢ​ያ​ትና በሐ​ዋ​ር​ያት መሠ​ረት ላይ ታን​ጻ​ች​ኋ​ልና የሕ​ን​ጻው የማ​ዕ​ዘን ራስ ድን​ጋ​ይም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በሐዋርያትና በነቢያትም መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑም ራስ ድንጋይ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 2:20
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በላ​ዩም ልክ ሆኖ የተ​ከ​ረ​ከመ ጥሩ ድን​ጋ​ይና የዝ​ግባ ሣንቃ ነበረ።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ስድ​ብ​ንና ነው​ርን ከእኔ አርቅ።


ጥበብ ለራስዋ ቤቷን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶዎችዋን አቆመች።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽ​ዮን ድን​ጋ​ይን ለመ​ሠ​ረት አስ​ቀ​ም​ጣ​ለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆ​ነ​ውን፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንና መሠ​ረቱ የጸ​ና​ውን የማ​ዕ​ዘን ድን​ጋይ አኖ​ራ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ያ​ምን አያ​ፍ​ርም።


ከእርሱ ዘንድ የማዕዘኑ ድንጋይ፥ ከእርሱም ዘንድ ችንካሩ፥ ከእርሱም ዘንድ የሰልፍ ቀስት፥ ከእርሱም ዘንድ አስገባሪው ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ።


እኔም እልሃለሁ፤ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚችም ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።


ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፤ ይህም ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፤’ የሚለውን ከቶ በመጽሐፍ አላነበባችሁምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የሾ​ማ​ቸው አስ​ቀ​ድሞ ሐዋ​ር​ያ​ትን፥ ሁለ​ተ​ኛም ነቢ​ያ​ትን፥ ሦስ​ተ​ኛም መም​ህ​ራ​ንን፥ ከዚ​ህም በኋላ ተአ​ም​ራ​ትና ኀይል ማድ​ረግ የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ ቀጥ​ሎም የመ​ፈ​ወስ ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ የመ​ር​ዳ​ትም ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን፥ የመ​ም​ራ​ትና ቋን​ቋን የመ​ና​ገር ሀብት የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ነው።


የሰ​ጠ​ኝ​ንም ጸጋ ዐው​ቀው አዕ​ማድ የሚ​ሏ​ቸው ያዕ​ቆ​ብና ኬፋ፥ ዮሐ​ን​ስም እኛ ወደ አሕ​ዛብ፥ እነ​ር​ሱም ወደ አይ​ሁድ እን​ድ​ን​ሄድ ለእ​ኔና ለበ​ር​ና​ባስ ቀኝ እጃ​ቸ​ውን ሰጡን።


በሌላ ዘመን ለሰው ልጆች ያል​ተ​ገ​ለጠ ዛሬ ለቅ​ዱ​ሳን ሐዋ​ር​ያ​ቱና ለነ​ቢ​ያቱ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እንደ ተገ​ለጠ፥


በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ።


በመጽሐፍ “እነሆ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና።


ለከተማይቱም ቅጥር ዐሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፤ በእነርሱም ውስጥ የዐሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች