Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መክብብ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ከእ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ቍጥር የላ​ቸ​ውም፤ በኋላ የሚ​መ​ጡት ግን በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም። ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በፊቱ የነበረው ሕዝብ ሁሉ ቍጥር ስፍር አልነበረውም፤ ከርሱ በኋላ የመጡት ግን በተተኪው አልተደሰቱም። ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከእርሱ በፊት የተገዙለት ሕዝብ ሁሉ ስፍር ቍጥር አልነበራቸውም፥ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህም ደግሞ ከንቱ፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ንጉሥ ሆኖ በሚያስተዳድርበት ጊዜ የሚገዛለት ሕዝብ ብዛት እጅግ ብዙ ነው፤ ከዙፋኑ ላይ በታጣ ጊዜ ግን ስላደረገው ነገር ሁሉ የሚያመሰግነው አንድ ሰው እንኳ አይገኝለትም፤ ይህም ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር የሚቈጠር ከንቱ ነገር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ከእርሱ በፊት የተገዙለት ሕዝብ ሁሉ አይቈጠሩም፥ በኋላ የሚመጡት ግን በእርሱ ደስ አይላቸውም። ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መክብብ 4:16
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከመ​ላው ነገደ እስ​ራ​ኤል የተ​ሰ​በ​ሰቡ ሕዝብ፥ “ንጉሡ ዳዊት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችን እጅ ታድ​ጎ​ናል፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ኖ​ናል፤ አሁ​ንም ስለ አቤ​ሴ​ሎም ከሀ​ገ​ሩና ከመ​ን​ግ​ሥቱ ሸሸ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ እር​ሱን ተከ​ት​ለው ወጡ፤ ከበ​ሮ​ንና መሰ​ን​ቆ​ንም መቱ፥ በታ​ላ​ቅም ደስታ ደስ አላ​ቸው፤ ከጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ምድር ተና​ወ​ጠች።


ከፀ​ሐይ በታች የተ​ሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


እጄ የሠ​ራ​ቻ​ትን ሥራ​ዬን ሁሉ፥ የደ​ከ​ም​ሁ​በ​ት​ንም ድካ​ሜን ሁሉ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነሆ፥ ሁሉ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነበረ፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ትርፍ አል​ነ​በ​ረም።


ከፀ​ሐ​ይም በታች የተ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በእኔ ላይ ክፉ ነውና ሕይ​ወ​ትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


እርሱ በፊቱ ደግ ለሆነ ሰው ጥበ​ብ​ንና ዕው​ቀ​ትን፥ ደስ​ታ​ንም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ለኀ​ጢ​አ​ተኛ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደግ ለሆነ ይሰጥ ዘንድ እን​ዲ​ሰ​በ​ስ​ብና እን​ዲ​ያ​ከ​ማች ጥረ​ትን ይሰ​ጠ​ዋል። ይህ ደግሞ ከንቱ፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።


ከፀ​ሓይ በታች የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሕያ​ዋን ሁሉ በእ​ርሱ ፋንታ ከሚ​ነ​ሣው ከሌ​ላው ጐል​ማሳ ጋር ሆነው አየሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች