Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው በእያንዳንዱ ቃል እንጂ፣ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ሊያስተምርህ አስራበህ፤ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቁትን መና መገበህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰው የሚኖረው በእንጀራ ብቻ ሳይሆን ከጌታ አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር ሊያሳውቅህ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በራብ እንድትሠቃይ አደረገህ፤ ቀጥሎም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ የማታውቁትን መና አበላህ፤ ይህንንም ማድረጉ ሰው ሕይወቱ ተጠብቆለት መኖር የሚችለው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አለመሆኑን ሊያስተምርህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፥ አንተም ያላወቅኸውን አባቶችህም ያላወቁትን መና አበላህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 8:3
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥ ርስ​ቱ​ንም ተጸ​የፈ።


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


እርሱም መልሶ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል” አለው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ሰው የሚ​ኖ​ረው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወ​ጣው ቃል ነው እንጂ በእ​ን​ጀራ ብቻ አይ​ደ​ለም የሚል ተጽ​ፎ​አል” አለው።


ሁሉም ያን መን​ፈ​ሳዊ ምግብ ተመ​ገቡ።


አርባ ዓመት በም​ድረ በዳ መራ​ችሁ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁም አላ​ረ​ጀ​ባ​ች​ሁም፤ ጫማ​ች​ሁም በእ​ግ​ራ​ችሁ ላይ አል​ተ​ቀ​ደ​ደም።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስ​ክ​ት​ደ​ርሱ ድረስ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ች​ሁም፤ የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ረ​ውን መጠ​ጥም አል​ጠ​ጣ​ች​ሁም።


ይህ ነገር ሕይ​ወ​ታ​ችሁ ነው እንጂ ለእ​ና​ንተ ከንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ በዚ​ህም ነገር ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ዘመ​ና​ችሁ ይረ​ዝ​ማል።”


ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች