Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ በጥ​ቂት በጥ​ቂቱ ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ምድ​ርም ምድረ በዳ እን​ዳ​ት​ሆን የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም እን​ዳ​ይ​በ​ዙ​ብህ ፈጥኜ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ አት​በል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 አምላክህ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት ከፊትህ ያስወጣቸዋል፤ የዱር አራዊቱ ቍጥር በአካባቢህ እንዳይበራከት ሁሉንም በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይፈቀድልህም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ጌታ አምላካችሁ እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት ከፊትህ ያስወጣቸዋል፤ የዱር አራዊት እንዳይበዙብህ፥ እነርሱን በአንድ ጊዜ ማጥፋት አይቻልህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አምላክህ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ጥቂት በጥቂት እየነቃቀለ ያስወጣቸዋል፤ እነርሱን ሁሉ በአንድ ጊዜ ማጥፋት አትችልም፤ ይህን ብታደርግ አራዊት በምድሪቱ ላይ በዝተው ያስቸግሩሃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 አምላክህም እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ በጥቂት በጥቂቱ ከፊትህ ያወጣቸዋል፤ የምድረ በዳ አራዊት እንዳይበዙብህ አንድ ጊዜ ታጠፋቸው ዘንድ አይገባህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 7:22
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚ​በላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በፊ​ት​ህም ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረህ ከፊ​ትህ ያር​ቃ​ቸ​ዋል፥ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ግን የይ​ሁዳ ልጆች ሊያ​ሳ​ድ​ዱ​አ​ቸው አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ ተቀ​ም​ጠ​ዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች