Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይልቅ የተ​ባ​ረ​ክህ ትሆ​ና​ለህ፤ ከሴ​ቶ​ችህ መካን አት​ኖ​ርም፤ ልጆች የሌ​ሏት አገ​ል​ጋ​ይም አት​ኖ​ርም፤ ከከ​ብ​ት​ህም መካን አይ​ኖ​ርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከሕዝቦች ሁሉ የበለጠ አንተ ትባረካለህ፤ ከአንተ ወይም ከከብቶችህ መካከል የማይወልድ ወንድ ወይም ሴት አይኖርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከሕዝቦች ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፥ ወንድ ይሁን ወይም ሴት በሰውህና በከብትህም ዘንድ መካን አይኖርብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የአንተን ያኽል በብዙ የተባረከ ሕዝብ በዓለም ላይ ከቶ አይገኝም፤ ከአንተ መካከል ወንድም ሆነ ሴት እንዲሁም ከእንስሶችህ መካከል መኻን አይገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረክህ ትሆናለህ፤ በሰውህና በከብትህም ዘንድ ወንድ ቢሆን ወይም ሴት ብትሆን መካን አይሆንብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 7:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


ወደ እና​ን​ተም እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ፤ አባ​ዛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃል ኪዳ​ኔ​ንም ከእ​ና​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በለ​ዓ​ምን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር አት​ሂድ፤ የተ​ባ​ረከ ነውና ሕዝ​ቡን አት​ር​ገም” አለው።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋን ይሰ​ጥህ ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ችህ በማ​ለ​ላ​ቸው በም​ድ​ርህ ላይ፥ በሆ​ድህ ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ ከብ​ቶ​ች​ህን በማ​ብ​ዛት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ​ነ​ቱን ያበ​ዛ​ል​ሃል።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ቡሩክ ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ባ​ቶ​ችህ ደስ እን​ዳ​ለው በመ​ል​ካሙ ነገር ሁሉ እንደ ገና በአ​ንተ ደስ ይለ​ዋ​ልና አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጅህ ሥራ ሁሉ፥ በሆ​ድ​ህም ፍሬ፥ በእ​ር​ሻ​ህም ፍሬ፥ በከ​ብ​ት​ህም ብዛት እጅግ ይባ​ር​ክ​ሃል።


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች