Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 5:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና፤ በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና እስከ አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፥ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩትን ሰዎች፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ የምበቀል ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ እነዚያን የተቀረጹ ምስሎች አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9-10 በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ ለሚወድዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኛና አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 5:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው፤ አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸ​ውም፤ አታ​ም​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም፤ አት​ሠ​ዉ​ላ​ቸ​ውም።


ስሙ ቀና​ተኛ የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅን​ዐት ያለው አም​ላክ ነውና ለሌላ አም​ላክ አት​ስ​ገድ።


ለብዙ ሺህ ጽድ​ቅን የሚ​ጠ​ብቅ፥ ቸር​ነ​ትን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ አበ​ሳ​ንና መተ​ላ​ለ​ፍን፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ይቅር የሚል፥ በደ​ለ​ኛ​ው​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም ኀጢ​አት በል​ጆች፥ እስከ ሦስ​ትና እስከ አራት ትው​ል​ድም በልጅ ልጆች የሚ​ያ​መጣ አም​ላክ ነው” ሲል አወጀ።


ታላ​ቅና ኀያል አም​ላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም በደል ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በል​ጆ​ቻ​ቸው ብብት ትመ​ል​ሳ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዓቱ የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበ​ሳን፥ መተ​ላ​ለ​ፍ​ንና ኀጢ​አ​ትን ይቅር የሚል፥ ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ከቶ የማ​ያ​ነጻ፥ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት እስከ ሦስ​ትና አራት ትው​ልድ ድረስ በል​ጆች ላይ የሚ​ያ​መጣ ነው።


እን​ዳ​ት​በ​ድሉ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል፥ የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ምሳሌ፥ በወ​ንድ ወይም በሴት መልክ የተ​ሠ​ራ​ውን፥ በም​ድር ላይ ያለ​ውን፥


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​በላ እሳት፥ ቀና​ተ​ኛም አም​ላክ ነውና።


በመ​ካ​ከ​ልህ ያለው አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀና​ተኛ አም​ላክ ነውና የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቁጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ብህ፥ ከም​ድ​ርም ፊት እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋህ ተጠ​ን​ቀቅ።


የሚ​ጠ​ሉ​ትን ለማ​ጥ​ፋት በፊ​ታ​ቸው ብድ​ራት ይመ​ል​ስ​ባ​ቸ​ዋል፤ ለሚ​ጠ​ላው አይ​ዘ​ገ​ይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድ​ራ​ትን ይመ​ል​ስ​በ​ታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች