Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በሐ​ሰት አት​ጥራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በሐ​ሰት የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን በደል አልባ አያደርገውምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ ‘የጌታን የአምላክህ ስም በከንቱ አትጥራ፥ ጌታ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሳይቀጣው አይቀርምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “ ‘የእኔን የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ሰው እግዚአብሔር ሳይቀጣው አይቀርም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 5:11
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


በስ​ሜም በሐ​ሰት አት​ማሉ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ቅዱስ ስም አታ​ር​ክሱ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል፤ በስ​ሙም ማል።


አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፤ እር​ሱ​ንም ብቻ አም​ልክ፤ እር​ሱ​ንም ተከ​ተል በስ​ሙም ማል።


ከሁሉም በፊት ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፤ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች