Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 3:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 እኔ እን​ድ​ሻ​ገ​ርና፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ያለ​ች​ውን መል​ካ​ሚ​ቱን ምድር፥ ያንም መል​ካ​ሙን ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር አንጢ ሊባ​ኖ​ስ​ንም እን​ዳይ ፍቀ​ድ​ልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አሁንም ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን ያችን መልካሚቱን ምድር፣ ውብ የሆነችውን ኰረብታማ አገርና ሊባኖስን እንዳይ ፍቀድልኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 እለምንሃለሁ፥ ልሻገር፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ጌታ ሆይ! የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሬ ከወንዙ ማዶ ያለችውን ውብና ኮረብታማ የሆነችውን ለምለሚቱን ምድርና የሊባኖስን ተራራ ማየት እንድችል ፍቀድልኝ።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 እኔ ልሻገር፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር ያንም መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ልይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 3:25
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።


በዚያ ቀን ከግ​ብፅ ምድር ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ቸው፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው፥ ከም​ድር ሁሉ ወደ​ም​ት​በ​ልጥ ምድር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጄን አነ​ሣሁ።


እኛስ በአ​ንተ ዘንድ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ርስት አድ​ር​ገህ ስጠን፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን አታ​ሻ​ግ​ረን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ አል​ሰ​ማ​ኝ​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘ይበ​ቃ​ሃል፤ በዚህ ነገር ደግ​መህ አት​ና​ገ​ረኝ።’


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች