Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 3:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ይህ​ች​ንም ምድር በዚ​ያን ዘመን ወረ​ስን፤ በአ​ር​ኖ​ንም ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የገ​ለ​ዓ​ድን ተራ​ራማ ሀገር እኩ​ሌታ፥ ከተ​ሞ​ቹ​ንም ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ ነገድ ሰጠ​ኋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በዚያ ጊዜ ከያዝነው ምድር ላይ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር አንሥቶ በስተሰሜን ያለውን ግዛት፣ በተጨማሪም ኰረብታማውን የገለዓድ አገር እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በዚያን ወቅት ይህችን ምድር በወረስን ጊዜ፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “ምድሪቱን ከወረስን በኋላ በአርኖን ወንዝ አጠገብ ካለችው ከዓሮዔር ከተማ ጀምሮ በስተ ሰሜን በኩል ያለውን ግዛትና የኮረብታማይቱን የገለዓድን እኩሌታ ከነከተሞችዋ ለሮቤልና ለጋድ ነገዶች ሰጠሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይህችንም ምድር በዚያን ዘመን ወረስን፤ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር ጀምሮ የገለዓድን ተራራማ አገር እኩሌታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገድ ሰጠኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 3:12
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዮ​ር​ዳ​ኖስ ምሥ​ራቅ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ሀገር ሁሉ፥ በአ​ር​ኖን ወንዝ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ የጋ​ድ​ንና የሮ​ቤ​ልን የም​ና​ሴ​ንም ሀገር፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን መታ።


ሙሴም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ገለ​ዓ​ድን ሰጠው፤ በእ​ር​ስ​ዋም ተቀ​መጠ።


በአ​ር​ኖን ሸለቆ አጠ​ገብ ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔ​ርና በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ካለ​ችው ከተማ ጀም​ረን እስከ ገለ​ዓድ ተራራ ድረስ ማን​ኛ​ዪ​ቱም ከተማ አላ​መ​ለ​ጠ​ች​ንም፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ችን ሰጠን።


የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን፥ የባ​ሳ​ንም ንጉሥ ዐግ ሊወ​ጉን ወጡ​ብን፤ እኛም መታ​ና​ቸው፤


ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወስ​ደን ለሮ​ቤ​ልና ለጋድ፥ ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ርስት አድ​ር​ገን ሰጠ​ና​ቸው።


ከገ​ለ​ዐ​ድም የቀ​ረ​ውን የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ባሳ​ንን ሁሉ፥ የአ​ር​ጎ​ብ​ንም ምድር ሁሉ ለም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ሰጠሁ፤ ያችም ባሳን ሁሉ የራ​ፋ​ይም ሀገር ተብላ ተቈ​ጠ​ረች።


በአ​ር​ኖን ወንዝ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ ኤር​ሞን ድረስ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች