Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የሚ​ሶ​ር​ንም ከተ​ሞች ሁሉ፥ የገ​ለ​ዓ​ድ​ንም ሁሉ፥ የባ​ሳ​ን​ንም ሁሉ እስከ ኤል​ከ​ድና እስከ ኤድ​ራ​ይን ድረስ በባ​ሳን የሚ​ኖር የዐ​ግን መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች ሁሉ ወሰ​ድን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በከፍታው ቦታ ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ገለዓድን እንዳለ፣ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ያለውን ባሳንን ሁሉ እንዲሁም በባሳን ውስጥ የሚገኙትን የዐግ ግዛት ከተሞች በእጃችን አደረግን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ ባሳንን ሁሉ፥ እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ድረስ፥ በባሳንም ያሉትን የዖግን መንግሥት ከተሞች ወሰድን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚህም ዐይነት የባሳን ንጉሥ የዖግ ግዛቶች የሆኑትን በደጋ የሚገኙትን ሳለካና ኤድረዒ ተብለው የሚጠሩትን ከተሞችና እንዲሁም የገለዓድንና የባሳንን አውራጃዎች ሁሉ ያዝን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ሰልካና እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 3:10
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ የጌ​ቤር ልጅ ነበረ፤ ለእ​ር​ሱም በገ​ለ​ዓድ ያሉት የም​ናሴ ልጅ የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ነበሩ፤ ለእ​ር​ሱም ደግሞ በባ​ሳን፥ በአ​ር​ጎብ ዳርቻ ያሉት ቅጥ​ርና የናስ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች የነ​በ​ረ​ባ​ቸው ስድሳ ታላ​ላቅ ከተ​ሞች ነበ​ሩ​በት፤


የጋ​ድም ልጆች በባ​ሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአ​ፋ​ዛ​ዣ​ቸው ተቀ​መጡ።


ተመ​ል​ሰ​ውም በባ​ሳን መን​ገድ ወጡ፤ የባ​ሳ​ንም ንጉሥ ዐግ ከሕ​ዝቡ ሁሉ ጋር በኤ​ድ​ራ​ይን ይወ​ጋ​ቸው ዘንድ ወጣ።


ለሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳ በደ​ል​ዳላ ስፍራ ያለ ባሶር፥ ለጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ያለ ራሞት፥ ለም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ያለ ጎላን ነበሩ።


በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ መሿ​ለ​ኪያ ካለው ከአ​ሴ​ዶን ተራራ በታች ያለ​ውን ዓረባ ሁሉ ወሰዱ።


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ በሸ​ለ​ቆው መካ​ከል ያለ​ችው ከተማ፥ ሜሶ​ርም ሁሉ፥


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ከመ​ሐ​ና​ይም ጀምሮ የባ​ሳን ንጉሥ የዐግ መን​ግ​ሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባ​ሳ​ንም ያሉት የኢ​ያ​ዕር መን​ደ​ሮች ሁሉ ስድ​ሳው ከተ​ሞች፥ የገ​ለ​ዓ​ድም እኩ​ሌታ፥


በባ​ሳ​ንም ያሉት የዐግ መን​ግ​ሥት ከተ​ሞች፥ አስ​ጣ​ሮ​ትና ኤድ​ራ​ይን ነበረ። እነ​ዚ​ህም ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች ሆኑ፤ ለም​ናሴ ልጅ ለማ​ኪር ልጆች እኩ​ሌ​ታም በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ይህ ነበረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች