Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 27:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ይረ​ግ​ሙም ዘንድ በጌ​ባል ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ሮቤ​ልና ጋድ፥ አሴ​ርና ዛብ​ሎን፥ ዳንና ንፍ​ታ​ሌም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳንና ንፍታሌምም በጌባል ተራራ ላይ ለመርገም ይቁሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ለእርግማንም በዔባል ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው ሮቤል፥ ጋድ፥ አሴር፥ ዛብሎን፥ ዳንና ንፍታሌምም ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ለእርግማንም በዔባል ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው የሮቤል፥ የጋድ፥ የአሴር፥ የዛብሎን፥ የዳንና የንፍታሌም ነገዶች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ይረግሙም ዘንድ እነዚህ፥ ሮቤልና ጋድ አሴርና ዛብሎን ዳንና ንፍታሌም፥ በጌባል ተራራ ላይ ይቁሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 27:13
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልያም ፀነ​ሰች፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች፥ ስሙ​ንም ሮቤል ብላ ጠራ​ችው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴን አይ​ቶ​አ​ልና፥ እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ ባሌ ይወ​ድ​ደ​ኛል” ስትል።


ልያም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካም ስጦ​ታን ሰጠኝ፤ እን​ግ​ዲ​ህስ ከዛሬ ጀምሮ ባሌ ይወ​ደ​ድ​ኛል ስድ​ስት ልጆ​ችን ወል​ጄ​ለ​ታ​ለ​ሁና” አለች፤ ስሙ​ንም ዛብ​ሎን ብላ ጠራ​ችው።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ አን​ተን ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​ባት ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፥ በረ​ከ​ቱን በገ​ሪ​ዛን ተራራ፥ መር​ገ​ሙ​ንም በጌ​ባል ተራራ ታኖ​ራ​ለህ።


“ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ሕዝ​ቡን ይባ​ርኩ ዘንድ በገ​ሪ​ዛን ተራራ ላይ የሚ​ቆሙ እነ​ዚህ ናቸው፤ ስም​ዖ​ንና ሌዊ፥ ይሁ​ዳና ይሳ​ኮር፥ ዮሴ​ፍና ብን​ያም።


ሌዋ​ው​ያ​ንም ከፍ ባለች ድምፅ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ይና​ገሩ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ፥ እነ​ዚ​ህን ድን​ጋ​ዮች በጌ​ባል ተራራ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሕዝብ አስ​ቀ​ድሞ ይባ​ር​ኩ​አ​ቸው ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ እን​ዳ​ዘዘ፥ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ውም፥ የሀ​ገሩ ልጆ​ችም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም እኩ​ሌ​ቶቹ በገ​ሪ​ዛን ተራራ አጠ​ገብ፥ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም በጌ​ባል ተራራ አጠ​ገብ ሆነው፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦተ ሕግ በተ​ሸ​ከ​ሙት በሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ፊት ለፊት፥ በታ​ቦ​ቱም ፊት በግ​ራና በቀኝ ቆመው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች