ዘዳግም 26:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ቃላችንን ሰማ፤ ጭንቀታችንንም፥ ድካማችንንም፥ ግፋችንንም አየ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰማ፤ ጕስቍልናችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ከዚያ በኋላ የአባቶቻችን አምላክ ወደ ሆነው ወደ ጌታ ጮኽን፤ ጌታም ጩኸታችንን ሰማ። ጉስቁልናችንን፥ ድካማችንንና መጨቆናችንን ተመለከተ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 እኛም ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ጩኸታችንን ሰምቶ ሥቃያችንን፥ ድካማችንንና መጨቈናችንን ተመለከተ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ድምፃችንን ሰማ፥ ጭንቀታችንንም ድካማችንንም ግፋችንንም አየ፤ ምዕራፉን ተመልከት |