Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 26:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ዛሬ አዝ​ዞ​ሃል፤ አን​ተም በፍ​ጹም ልብ​ህና በፍ​ጹም ነፍ​ስህ ጠብ​ቀው፤ አድ​ር​ገ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዐትና ሕግ ትጠብቅ ዘንድ ዛሬ ያዝዝሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህ፣ በፍጹምም ነፍስህ ትፈጽመው ዘንድ ተጠንቀቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 “አምላክህ ጌታ ይህን ሥርዓትና ሕግ እንድትጠብቅ ዛሬ ያዝሃል፤ ስለዚህ አንተም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ለመፈጸም ተጠንቀቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 “እግዚአብሔር አምላክህ ሕጎችንና ሥርዓቶችን እንድትጠብቅ እነሆ፥ ዛሬ ያዝሃል፤ ስለዚህ በፍጹም ልብህና ነፍስህ ጠብቃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ሥርዓትና ፍርድ ታደርግ ዘንድ ዛሬ አዝዞሃል፤ አንተም በፍጹም ልብህና በፍጹም ነፍስህ ጠብቀው፥ አድርገውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 26:16
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አሁ​ንስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ የሚ​ፈ​ል​ገው ምን​ድን ነው? አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈራ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ ታመ​ል​ከው ዘንድ ነው እንጂ፥


“አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ውደድ፤ ሕጉ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም፥ ፍር​ዱ​ንም በዘ​መ​ንህ ሁሉ ጠብቅ።


“በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበ​ዙም ዘንድ፥ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን የም​ት​ሻ​ገ​ሩ​ላ​ትን ምድር እን​ድ​ት​ወ​ር​ሷት ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤


“በም​ድር ላይ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሷት ዘንድ በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ሀገር ታደ​ር​ጉት ዘንድ የም​ት​ጠ​ብ​ቁት ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።


“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።


አን​ተም በመ​ን​ገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን፥ ፍር​ዱ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ትሰማ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ክህ እን​ዲ​ሆን ዛሬ መር​ጠ​ሃል።


ነገር ግን ከዚያ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትሻ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ በል​ብ​ህም ሁሉ፥ በነ​ፍ​ስ​ህም ሁሉ​የ​ፈ​ለ​ግ​ኸው እንደ ሆነ ታገ​ኘ​ዋ​ለህ።


“ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ታደ​ር​ጉት ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።


ለአ​ንተ ያዘ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ፥ ምስ​ክ​ሩ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም አጥ​ብ​ቀህ ጠብቅ።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ፥ በፍ​ጹ​ምም ኀይ​ልህ ውደድ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች