Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “ዐሥ​ራት በም​ታ​ወ​ጣ​በት በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ሁሉ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በፈ​ጸ​ምህ ጊዜ፥ ሁለ​ተኛ ዐሥ​ራት አው​ጥ​ተህ በከ​ተ​ሞ​ችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠ​ግ​ቡም ዘንድ ለሌ​ዋ​ዊው፥ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም፥ ለድሃ-አደ​ጉም፥ ለመ​በ​ለ​ቲ​ቱም ስጣ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የዐሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ምርት አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፣ ለሌዋዊው፣ ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “አሥራት በምታወጣት በሦስተኛው ዓመት ከምርትህ አንድ ዐሥረኛ ለይተህ ካወጣህ በኋላ በየከተሞችህ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ስጣቸው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “በሦስተኛው ዓመት ማለት ዐሥራት በምታወጣት ዓመት ዐሥራትህን ሁሉ አጠናቅቀህ ከሰበሰብክ በኋላ በከተማህ ለሚገኙ ለሌዋውያን፥ ለመጻተኞች፥ ለሙት ልጆችና ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች ሰጥተህ ጠግበው እንዲበሉ አድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የፍሬህን ሁሉ አሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ በአገርህ ደጅ ውስጥ ይበሉ ዘንድ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው ለመጻተኛውም ለድሀ አደጉም ለመበለቲቱም ስጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 26:12
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”


ዮሴ​ፍም ለፈ​ር​ዖን ካል​ሆ​ነ​ችው ከካ​ህ​ናቱ ምድር በቀር አም​ስ​ተ​ኛው እጅ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲ​ሆን በግ​ብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደ​ረ​ጋት።


ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ ለድሃ የሚራራ ግን ብፁዕ ነው።


“የም​ድ​ርም ዐሥ​ራት፥ ወይም የም​ድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ነው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ገው የሚ​ለ​ዩ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ለሌ​ዋ​ው​ያን ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ርስት አት​ወ​ር​ሱም አል​ኋ​ቸው።”


አን​ተም፥ ወንድ ልጅ​ህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪ​ያ​ህና ሴት ባሪ​ያህ፥ በሀ​ገ​ር​ህም ውስጥ ያለ ሌዋ​ዊና መጻ​ተኛ፥ ድሃ-አደ​ግና መበ​ለ​ትም በበ​ዓ​ልህ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


ከሌዊ ልጆ​ችም፥ ክህ​ነ​ትን የሚ​ቀ​በ​ሉት ከሕ​ዝቡ ማለት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እነ​ርሱ ምንም ከአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ቢወጡ ከእ​ነ​ርሱ ዐሥ​ራ​ትን በሕግ እን​ዲ​ያ​ስ​ወጡ ትእ​ዛዝ አላ​ቸው።


እንደ ተነ​ገ​ረም ዐሥ​ራ​ትን የሚ​ቀ​በል ሌዊ ስን​ኳን በአ​ብ​ር​ሃም በኩል ዐሥ​ራ​ትን ሰጠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች