Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 23:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “አሞ​ናዊ ወይም ሞዓ​ባዊ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤ እስከ ዐሥር ትው​ልድ ድረስ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማንኛውም የርሱ ዘር፣ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳን ቢሆን ወደ ጌታ ጉባኤ አይግባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ዐሞናዊም ሆነ ሞአባዊ ወይም የእነርሱ ዘር የሆነ ሁሉ እስከ ዐሥር ትውልድ እንኳ የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ አባል አይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3-4 ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ እንጀራና ውኃ ይዘው በመንገድ ላይ አልተቀበሉአችሁምና፥ በመስጴጦምያ ካለው ከፋቱራ የቢዖርን ልጅ በለዓምን ዋጋ ሰጥተው ይረግምህ ዘንድ አምጥተውብሃልና አሞራዊና ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ለዘላለም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 23:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ​ሞም በዚያ ወራት የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ሞ​ንን፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም ሴቶች ያገ​ቡ​ትን አይ​ሁድ አየሁ።


አሞ​ና​ዊ​ውም ጦቢያ ወደ እርሱ ቀርቦ፥ “በድ​ን​ጋይ በሚ​ሠ​ሩት ቅጥ​ራ​ቸው ላይ ቀበሮ ቢወ​ጣ​በት ያፈ​ር​ሰ​ዋል” አለ።


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጦብ​ያም፥ ዓረ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አሞ​ና​ው​ያ​ንም፥ አዛ​ጦ​ና​ው​ያ​ንም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅጥር እየ​ታ​ደሰ እንደ ሄደ፥ የፈ​ረ​ሰ​ውም ሊጠ​ገን እንደ ተጀ​መረ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ጠጋ መጻ​ተኛ፥ “በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሕ​ዝቡ ይለ​የ​ኛል” አይ​በል፤ ጃን​ደ​ረ​ባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይ​በል።


ስለ አሞን ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሚል​ኮም ጋድን ይወ​ርስ ዘንድ ሕዝ​ቡም በከ​ተ​ሞቹ ላይ ይቀ​መጥ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሉ​ት​ምን? ወይስ ወራሽ የለ​ው​ምን?


ዮድ። አስ​ጨ​ና​ቂው በም​ኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባ​ኤህ እን​ዳ​ይ​ገቡ ያዘ​ዝ​ሃ​ቸው አሕ​ዛብ ወደ መቅ​ደ​ስዋ ሲገቡ አይ​ታ​ለ​ችና።


“ ‘ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።


ዲቃላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አይ​ግባ፤


የቅርብ ዘመዱም፦ የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መቤዠት አልችልም፣ እኔ መቤዠቱን አልችልምና አንተ ከእኔ መቤዠቱን ውሰደው አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች