Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 2:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 የሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳ​ል​ፈን ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን አደ​ን​ድ​ኖ​ታ​ልና፥ ልቡ​ንም አጽ​ን​ቶ​ታ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ይሁን እንጂ የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላካችሁ እግዚአብሔር አሁን እንዳደረገው ሁሉ እርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ለመስጠት መንፈሱን አደንድኖት፣ ልቡንም አጽንቶት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 “የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፥ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ፥ ጌታ አምላካችሁ መንፈሱን አደንድኖታልና ልቡንም አጽንቶታልና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 “ነገር ግን ሲሖን ንጉሥ ሴዎን በእርሱ ግዛት ውስጥ አልፈን እንድንሄድ ባለመፍቀዱ፥ አሁን እንዳደረገው አምላካችሁ እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሊሰጠው ስለ ፈቀደ ትዕቢተኛና እልኸኛ አደረገው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና፥ ልቡንም አጽንቶታልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 2:30
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ አፍ ለና​ባጥ ልጅ ለኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሴ​ሎ​ና​ዊው በአ​ኪያ ቃል ስለ ናባጥ ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃሉን እን​ዲ​ያ​ጸና ለውጡ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነበ​ርና ንጉሡ ሕዝ​ቡን አል​ሰ​ማም።


ሙሴና አሮ​ንም እነ​ዚ​ህን ተአ​ም​ራ​ቶ​ችና ድን​ቆች ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ለመ​ል​ቀቅ እንቢ አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ይ​ለ​ቅቅ የፈ​ር​ዖን ልብ ደነ​ደነ።


አንተ እል​ከኛ፥ አን​ገ​ት​ህም የብ​ረት ጅማት፥ ግን​ባ​ር​ህም ናስ እንደ ሆነ ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤


የልብ ሕማ​ም​ንና ርግ​ማ​ን​ህን ስጣ​ቸው።


ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በወ​ሰኑ ላይ ያልፉ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም፤ ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ለመ​ው​ጋት ወደ ምድረ በዳ ወጣ፤ ወደ ኢያ​ሶ​ንም መጣ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ተዋ​ጋ​ቸው።


ተመ​ል​ሰ​ውም በባ​ሳን መን​ገድ ወጡ፤ የባ​ሳ​ንም ንጉሥ ዐግ ከሕ​ዝቡ ሁሉ ጋር በኤ​ድ​ራ​ይን ይወ​ጋ​ቸው ዘንድ ወጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አሳ​ልፌ በእ​ጅህ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራው፤ በሐ​ሴ​ቦ​ንም በተ​ቀ​መ​ጠው በአ​ሞ​ሬ​ዎን ንጉሥ በሴ​ዎን እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እን​ዲሁ ታደ​ር​ግ​በ​ታ​ለህ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ‘የሐ​ሴ​ቦ​ንን ንጉሥ አሞ​ራ​ዊ​ውን ሴዎ​ን​ንና ምድ​ሩን በፊ​ትህ በእ​ጅህ አሳ​ልፌ መስ​ጠት እነሆ፥ ጀመ​ርሁ፤ ምድ​ሩን ትገዛ ዘንድ መው​ረስ ጀምር’ አለኝ።


ሴዎ​ንም እስ​ራ​ኤል በድ​ን​በሩ እን​ዲ​ያ​ልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በኢ​ያ​ሴ​ርም ሰፈረ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ተዋጋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች