Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሖራ​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ቸው አጥ​ፍቶ በሴ​ይር ለተ​ቀ​መ​ጡት ለዔ​ሳው ልጆች እን​ዳ​ደ​ረገ እነ​ርሱ ወረ​ሱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ እስከ ዛሬ ድረስ ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር ሖሪውያንን ከፊታቸው ባጠፋ ጊዜ፣ በሴይር ለሚኖሩት የዔሳው ዘሮች ያደረገው ይህንኑ ነበር። እነርሱም አሳድደው በማስወጣት ባስለቀቁት ስፍራ ላይ እስከ ዛሬ ይኖራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ፥ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ፥ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፥ እነርሱንም ቀምተው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እግዚአብሔር ኮረብታማ በሆነችው በኤዶም ለሚኖሩት ለዔሳው ዘሮችም እንደዚሁ አድርጎላቸው ነበር፤ ይኸውም ቀድሞ የኖሩባትን ሖራውያንን ደምስሶ እስከ አሁን የሚኖሩባትን ምድራቸውን ኤዶማውያን ወርሰው እንዲሰፍሩባት አድርጎአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 2:22
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሴ​ይር ተራ​ራ​ዎች ያሉ የኬ​ሬ​ዎስ ሰዎ​ች​ንም በበ​ረሃ አጠ​ገብ እስከ አለ​ችው እስከ ፋራን ዛፍ ድረስ መቱ​አ​ቸው።


ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።


ሖራ​ው​ያ​ንም ደግሞ አስ​ቀ​ድሞ በሴ​ይር ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ የዔ​ሳው ልጆች ግን መቱ​አ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ጠው በር​ስቱ ምድር እስ​ራ​ኤል እን​ዳ​ደ​ረገ፥ በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


እነ​ር​ሱም እንደ ዔና​ቃ​ው​ያን ታላ​ቅና ብዙ፥ ጽኑ​ዓ​ንም ሕዝብ ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም አሳ​ድ​ደው በስ​ፍ​ራ​ቸው ተቀ​መጡ።


የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች