Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 19:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድድ ዘንድ፥ ሁል​ጊ​ዜም በመ​ን​ገዱ ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ታደ​ር​ጋት ዘንድ ብት​ሰማ፥ በእ​ነ​ዚህ በሦ​ስት ከተ​ሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተ​ሞ​ችን ትጨ​ም​ራ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድና ምን ጊዜም በመንገዱ እንድትሄድ ዛሬ የማዝዝህን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቅ ከሆነ፣ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ጌታን እግዚአብሔርን እንድትወድና ምንጊዜም በመንገዱ እንድትሄድ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ እምትጠብቅ ከሆነ፥ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች ሁሉ በመፈጸም እግዚአብሔር አምላክህን ብትወድና በመንገዱ ብትሄድ ይህችን ምድር ስለሚሰጥህ ሌሎች ሦስት የመጠለያ ከተሞች ጨምረህ ሥራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9-10 አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ ሁልጊዜም በመንገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ዛሬ የማዝዝህን ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ታደርጋት ዘንድ ብትጠብቅ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ውስጥ ንጹሕ ደም እንዳይፈስስ ደምም በአንተ ላይ እንዳይሆን፥ በእነዚህ በሦስት ከተሞች ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 19:9
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።


አም​ላ​ክ​ህ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ስህ፥ በፍ​ጹ​ምም ኀይ​ልህ ውደድ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች