Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አንተ የም​ት​ወ​ር​ሳ​ቸው እነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሞራ ገላ​ጮ​ች​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችን ያዳ​ም​ጣሉ፤ ለአ​ንተ ግን እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ፈ​ቀ​ደ​ምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፣ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያደምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ አምላክህ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን ይህን እንድታደርግ ጌታ እግዚአብሔር አልፈቀደልህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሀገራቸውን አስለቅቀህ የምትወርስባቸው ሕዝቦች ሟርተኝነትንና ጥንቈላን ይወዳሉ፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላክህ ይህን እንድታደርግ አይፈቅድም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የምትወርሳቸው እነዚህ አሕዛብ ሞራ ገላጮችንና ምዋርተኞችን ያዳምጣሉ፤ አንተ ግን እንዲሁ ታደርግ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ከልክሎሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 18:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም አለው፥ “ይህን በል​ብህ ቅን​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግህ እኔ ዐወ​ቅሁ፤ እኔም ደግሞ በፊቴ ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ት​ሠራ ጠበ​ቅ​ሁህ፤ ስለ​ዚ​ህም ትቀ​ር​ባት ዘንድ አል​ተ​ው​ሁ​ህም።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


ሕዝ​ቡን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ትቶ​አ​ልና፤ ምድ​ራ​ቸው እንደ ቀድ​ሞው እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ምድር በሟ​ርት ተሞ​ል​ቶ​አ​ልና፤ እንደ ባዕድ ልጆ​ችም ሆነ​ዋ​ልና፤ ብዙ እን​ግ​ዶች ልጆ​ችም ተወ​ል​ደ​ው​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


እና​ንተ ግን፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አት​ገ​ዙም የሚ​ሉ​አ​ች​ሁን የሐ​ሰት ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንና ምዋ​ር​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕልም ዐላ​ሚ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ባለ ራእ​ዮ​ቻ​ች​ሁን፥ መተ​ተ​ኞ​ቻ​ች​ሁ​ንም አት​ስሙ፤


መተትንም ከእጅህ አጠፋለሁ፥ ምዋርተኞችም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆኑልህም፥


አሕ​ዛ​ብን ሁሉ በቀ​ድሞ ዘመን እንደ ነበ​ሩ​በት እንደ ጠባ​ያ​ቸው ሊኖሩ ተዋ​አ​ቸው።


ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን በእ​ሳት የሚ​ሠዋ፥ ምዋ​ር​ተ​ኛም፥ ሞራ ገላ​ጭም፥ አስ​ማ​ተ​ኛም፥ መተ​ተ​ኛም፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች