Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 18:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይህ​ንም የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የተ​ጠላ ነው፤ ስለ​ዚ​ህም ርኵ​ሰት አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነውና። ከእነዚህ አስጸያፊ ልምዶች የተነሣም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነውና፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣም ጌታ እግዚአብሔር እነዚያን አሕዛብ ከፊትህ ያባርራቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህን የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላና አጸያፊ ነው፤ አንተ ወደ ፊት በተራመድህ ቊጥር አምላክህ እግዚአብሔር አሕዛብን ከፊትህ ነቃቅሎ የሚያሳድድበት ምክንያት ይህንኑ ዐይነት የረከሰ ሥራ በማድረጋቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው፤ ስለዚህም ርኩሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 18:12
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ​ሞም ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈ​ውን የሕ​ጉን ቃል ያጸና ዘንድ፥ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ቹ​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ቹን ተራ​ፊ​ም​ንና ጣዖ​ታ​ት​ንም በይ​ሁዳ ሀገ​ርና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ገ​ኘ​ውን ርኵ​ሰት ሁሉ ኢዮ​ስ​ያስ አስ​ወ​ገደ።


በአ​ሕ​ዛ​ብም አለ​ቆች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም እንደ ክፋቱ መጠን ያደ​ር​ግ​በ​ታል፤ እኔም አሳ​ድ​ደ​ዋ​ለሁ።


“ከፊ​ታ​ችሁ የማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው አሕ​ዛብ በእ​ነ​ዚህ ሁሉ ረክ​ሰ​ዋ​ልና በእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ አት​ር​ከሱ።


ምድ​ሪ​ቱም ረከ​ሰች፤ ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ቷን በእ​ር​ስዋ ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትተ​ፋ​ለች።


ከእ​ና​ንተ በፊት የነ​በ​ሩት የሀ​ገሩ ልጆች ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ታ​ልና፤


ድር​ሻና ርስት ከአ​ንተ ጋር ስለ​ሌ​ለው በከ​ተ​ማህ ውስጥ ያለ​ውን ሌዋዊ ቸል አት​በል።


“ሴት የወ​ንድ ልብስ አት​ል​በስ፤ ወን​ድም የሴት ልብስ አይ​ል​በስ፤ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ ነውና።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ ከፊ​ትህ ባወ​ጣ​ቸው ጊዜ፦ ስለ ጽድቄ እወ​ር​ሳት ዘንድ ወደ​ዚች መል​ካም ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ባኝ ብለህ በል​ብህ አት​ና​ገር፤


ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባው ስለ ጽድ​ቅ​ህና ስለ ልብህ ቅን​ነት አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊ​ትህ በሚ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው በእ​ነ​ዚያ አሕ​ዛብ ኀጢ​አት ምክ​ን​ያ​ትና ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ቃል ያጸና ዘንድ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች