ዘዳግም 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ ሰባተኛው ቀን ግን መውጫው ስለሆነ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓል ይሁን፤ ለነፍስም ከሚሠራው በቀር ሥራን ሁሉ አታድርግበት። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ለስድስት ቀን እርሾ የሌለበት ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ አድርግ፤ ሥራም አትሥራበት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ስድስት ቀን ያልቦካ ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለጌታ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በሚከተሉት ስድስት ቀኖች ደግሞ እርሾ ሳይነካው የተዘጋጀ ቂጣ ትበላለህ፤ በሰባተኛው ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትሰግድ ዘንድ ጉባኤ ይሁን፤ በዚያ ቀን ሥራ አትሥራበት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ስድስት ቀን ቂጣ እንጀራ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ጉባኤ ይሁን፤ ሥራን ሁሉ አታድርግበት። ምዕራፉን ተመልከት |