Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 4:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይህ​ችን መል​እ​ክት እና​ንተ አን​ብ​ባ​ችሁ፥ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ያነ​ብ​ቡ​አት ዘንድ ወደ ሎዶ​ቅያ ላኩ​አት፤ ዳግ​መ​ኛም እና​ንተ ከሎ​ዶ​ቅያ የጻ​ፍ​ኋ​ትን መል​እ​ክት አን​ብ​ቡ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ይህች መልእክት ከተነበበችላችሁ በኋላ በሎዶቅያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ደግሞ በሎዶቅያ ያለችውን መልእክት አንብቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ይህም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበ በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንዲነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምታገኙትን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህችን መልእክት እናንተ ካነበባችኋት በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ይህችም መልእክት በእናንተ ዘንድ ከተነበበች በኋላ፥ በሎዶቅያ ሰዎች ማኅበር ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ ከሎዶቅያም የምትገኘውን መልእክት እናንተ ደግሞ አንብቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 4:16
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤር​ም​ያ​ስም ሠራ​ያን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ባቢ​ሎን በገ​ባህ ጊዜ እይ፤ ይህ​ንም ቃል ሁሉ አን​ብ​ብና፦


ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ።


እጅግ እን​ደ​ሚ​ወ​ዳ​ች​ሁና ስለ እና​ንተ በሎ​ዶ​ቅ​ያና በኢ​ያራ ከተማ ስላ​ሉ​ትም እን​ደ​ሚ​ቈ​ረ​ቈር እኔ ምስ​ክሩ ነኝ።


በሎ​ዶ​ቅያ ላሉት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና ለን​ም​ፋን፥ በቤ​ቱም ላለች ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ሰላ​ምታ አቅ​ር​ቡ​ልኝ።


ይህ መልእክት ለቅዱሳን ወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አምላችኋለሁ።


በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፤ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች