አሞጽ 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “እኔ ከምድር አሕዛብ ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “ከምድር ወገን ሁሉ፣ እናንተን ብቻ መረጥሁ፤ ስለዚህ ስለ ሠራችሁት ኀጢአት ሁሉ፣ እኔ እቀጣችኋለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 እንዲህም ይላል፦ “እኔ ከምድር ወገኖች ሁሉ እናንተን ብቻ አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “በዓለም ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የመረጥኩት እናንተን ብቻ ነው፤ በምትሠሩት ኃጢአት ሁሉ የምቀጣችሁ ስለዚህ ነው።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 እንዲህም ብሎአል፦ እኔ ከምድር ወገን ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፥ ስለዚህ ስለ ኃጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |