Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




አሞጽ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “እና​ንተ ግን ለእኔ የተ​ለ​ዩ​ትን የወ​ይን ጠጅ አጠ​ጣ​ች​ኋ​ቸው፤ ነቢ​ያ​ቱ​ንም፥ “ትን​ቢ​ትን አት​ና​ገሩ ብላ​ችሁ ከለ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም ትንቢት እንዳይናገሩ አዘዛችኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችሁ፤ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ፥ ብላችሁ አዘዛችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እናንተ ግን ናዝራውያንን የወይን ጠጅ በማጠጣት አሳታችሁ፤ ነቢያትንም ትንቢት እንዳይናገሩ ከለከላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እናንተ ግን ናዝራውያኑን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፥ ነቢያቱንም፦ ትንቢትን አትናገሩ ብላችሁ አዘዛችኋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




አሞጽ 2:12
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነቢ​ያ​ትን፥ “አት​ን​ገ​ሩን፤ ባለ ራእ​ዮ​ች​ንም አታ​ው​ሩን፤ ነገር ግን ሌላ​ውን ስሕ​ተት አስ​ረ​ዱን፤ ንገ​ሩ​ንም” ይላሉ፤


ስለ​ዚ​ህም፥ “በእ​ጃ​ችን እን​ዳ​ት​ሞት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ትን​ቢት አት​ና​ገር” ብለው ነፍ​ሴን ስለ​ሚሹ ስለ አና​ቶት ሰዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


በሬ​ካ​ባ​ው​ያ​ንም ልጆች ፊት የወ​ይን ጠጅ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ማድ​ጋ​ዎ​ች​ንና ጽዋ​ዎ​ችን አኑሬ፥ “የወ​ይ​ኑን ጠጅ ጠጡ” አል​ኋ​ቸው።


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትን​ቢት አት​ና​ገር፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቤት አት​ዘ​ብ​ዝ​ባ​ቸው ብለ​ሃል።


ትንቢት አትናገሩ ብለው ይናገራሉ፥ በእነዚህ ላይ ትንቢት አይናገሩም፥ ስድብም አይርቅም።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤ ወንድ ወይም ሴት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን የተ​ለየ ያደ​ርግ ዘንድ ልዩ ስእ​ለት ቢሳል፥


ከወ​ይን ጠጅና ከሚ​ያ​ሰ​ክር መጠጥ ራሱን የተ​ለየ ያድ​ርግ፤ ከወ​ይን ወይም ከሌላ ከሚ​ያ​ሰ​ክር ነገር የሚ​ገ​ኘ​ውን ሆም​ጣጤ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም ጭማቂ አይ​ጠጣ፤ የወ​ይ​ንም እሸት ወይም ዘቢብ አይ​ብላ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች