Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችም በዮ​ሴፍ ላይ ቀን​ተው ወደ ግብፅ ሀገር ሸጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከእ​ርሱ ጋር ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “የነገድ አባቶችም በዮሴፍ ቀንተው በባርነት ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከርሱ ጋራ ስለ ነበር፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “የአባቶችም አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብጽ ሸጡት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “የያዕቆብ ልጆች በወንድማቸው በዮሴፍ ላይ ቀንተው በግብጽ አገር ባሪያ እንዲሆን ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የአባቶችም አለቆች በዮሴፍ ቀንተው ወደ ግብፅ ሸጡት፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 7:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዮ​ሴፍ ጋር ነበር፤ ሥራ​ውም የተ​ከ​ና​ወ​ነ​ለት ሰው ሆነ፤ በግ​ብ​ፃ​ዊው ጌታ​ውም ቤት ተሾመ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በቤቱ ባለ​ውም ሁሉ ላይ ከሾ​መው በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ፃ​ዊ​ውን ቤት በዮ​ሴፍ ምክ​ን​ያት ባረ​ከው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በረ​ከት በቤ​ቱም፥ በእ​ር​ሻ​ውም ባለው ሁሉ ላይ ሆነ።


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ወደ እኔ ቅረቡ” አላ​ቸው። ወደ እር​ሱም ቀረቡ። እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ግብፅ የሸ​ጣ​ች​ሁኝ እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ።


ምድር ተከ​ፈ​ተች፥ ዳታ​ን​ንም ዋጠ​ችው፥ የአ​ቤ​ሮ​ን​ንም ወገን ደፈ​ነች፤


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


በውኃ ውስጥ ባለ​ፍህ ጊዜ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ ወን​ዞ​ችም አያ​ሰ​ጥ​ሙ​ህም፤ በእ​ሳ​ትም ውስጥ በሄ​ድህ ጊዜ አት​ቃ​ጠ​ልም፤ ነበ​ል​ባ​ሉም አይ​ፈ​ጅ​ህም።


አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፥ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱና ሥሩ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና።


ፍቅር ያስ​ታ​ግ​ሣል፤ ፍቅር ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ናል፤ ፍቅር አያ​ቀ​ና​ናም፤ ፍቅር አያ​ስ​መ​ካም፤ ፍቅር ልቡ​ናን አያ​ስ​ታ​ብ​ይም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች