Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሐዋርያት ሥራ 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከእ​ናቱ ማኅ​ፀ​ንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተ​ወ​ለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅ​ደ​ስም ከሚ​ገ​ቡት ምጽ​ዋት ይለ​ምን ዘንድ ሁል​ጊዜ እየ​ተ​ሸ​ከሙ መል​ካም በሚ​ል​ዋት በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ያስ​ቀ​ም​ጡት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት እንዲለምን፣ ሰዎች በየዕለቱ ተሸክመው “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ የሚያስቀምጡት አንድ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እዚያ “ውብ” እየተባለ የሚጠራ በር ነበር፤ ሲወለድ ጀምሮ ሽባ የሆነውን አንድ ሰው ሰዎች በየቀኑ እያመጡ እዚያ ያስቀምጡት ነበር፤ እርሱ እዚያ ተቀምጦ ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት ይለምን ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሐዋርያት ሥራ 3:2
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቍ​ስል ሕመም ተይዞ በባ​ለ​ጸ​ጋው ደጅ የወ​ደቀ አል​ዓ​ዛር የሚ​ባል አንድ ድሃም ነበረ።


ከዚ​ህም በኋላ ኢያ​ሪኮ በደ​ረሱ ጊዜ አንድ ዕውር በጎ​ዳና ተቀ​ምጦ ይለ​ምን ነበር።


ጎረ​ቤ​ቶ​ቹና ቀድሞ የሚ​ያ​ው​ቁት፥ ሲለ​ም​ንም ያዩት የነ​በ​ሩት ግን፥ “ይህ በመ​ን​ገድ ተቀ​ምጦ ይለ​ምን የነ​በ​ረው አይ​ደ​ለም?” አሉ።


እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ቆር​ኔ​ሌ​ዎስ ሆይ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጸሎ​ትህ ተሰማ፤ ምጽ​ዋ​ት​ህም ታሰ​በ​ልህ።


ወደ​እ​ር​ሱም ተመ​ል​ክቶ ፈራና፥ “አቤቱ፥ ምን​ድን ነው?” አለ፤ መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ጸሎ​ት​ህም ምጽ​ዋ​ት​ህም መል​ካም መታ​ሰ​ቢያ ሆኖ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐር​ጎ​አል።


በል​ስ​ጥ​ራ​ንም እግሩ የሰ​ለለ፥ ከእ​ና​ቱም ማኅ​ፀን ጀምሮ ሽባ የሆነ፥ ከቶም ሂዶ የማ​ያ​ውቅ አንድ ሰው ተቀ​ምጦ ነበር።


እር​ሱም መል​ካም በም​ት​ባ​ለው በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ምጽ​ዋት ይለ​ምን የነ​በ​ረው እንደ ሆነ ዐወ​ቁት፤ በእ​ር​ሱም ከሆ​ነው የተ​ነሣ መገ​ረ​ምና መደ​ነቅ ሞላ​ባ​ቸው።


ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች