ሐዋርያት ሥራ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 የእግዚአብሔር መልአክም በራእይ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት በግልጥ ታየው፤ ወደ እርሱም ገብቶ፥ “ቆርኔሌዎስ ሆይ፥” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 አንድ ቀን፣ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ የእግዚአብሔር መልአክ በራእይ ወደ እርሱ መጥቶ፣ “ቆርኔሌዎስ ሆይ!” ሲለው በግልጽ አየ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል “ቆርኔሌዎስ ሆይ!” የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 አንድ ቀን በዘጠኝ ሰዓት ገደማ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባና “ቆርኔሌዎስ!” ብሎ ሲጠራው በራእይ በግልጥ ታየው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፦ “ቆርኔሌዎስ ሆይ” የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው። ምዕራፉን ተመልከት |