Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 19:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ ለእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች መል​ሰው፥ “ንጉሡ ለእኛ ቅር​ባ​ችን ነው፤ ስለ​ምን በዚህ ነገር ትቈ​ጣ​ላ​ችሁ? በውኑ ከን​ጉሡ አን​ዳች በል​ተ​ና​ልን? ወይስ እርሱ በረ​ከት ሰጥ​ቶ​ና​ልን? ወይስ ጭፍራ አድ​ርጎ ሾመ​ንን?” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፣ ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለ ሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቈጣ ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው፥ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን በሹልክታ ለብቻቸው ይዘው እርሱንና ቤተሰቡን ከተከታዮቹ ጋር ዮርዳኖስን ለምን አሻገሩ?” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 የይሁዳም ሰዎች “እኛ ይህን ያደረግነው ንጉሡ የእኛ ወገን ስለ ሆነ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ እናንተስ በዚህ ነገር ስለምን ትቈጣላችሁ? እርሱ ለምግባችን ምንም የከፈለን ነገር የለም፤ ሌላም ምንም ነገር አልሰጠንም” ሲሉ መለሱላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 የይሁዳም ሰዎች ሁሉ ለእስራኤል ሰዎች መልሰው፦ ንጉሡ ለእኛ ቅርባችን ነው፥ ስለ ምን በዚህ ነገር ትቆጣላችሁ? በውኑ ከንጉሡ አንዳች በልተናልን? ወይስ እርሱ በረከት ሰጥቶናልን? አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 19:42
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ ወን​ድ​ሞች፥ የአ​ጥ​ንቴ ፍላ​ጭና የሥ​ጋዬ ቍራጭ ናችሁ፤ እና​ንተ ንጉ​ሡን ወደ ቤቱ ከመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዘገ​ያ​ችሁ?


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ለይ​ሁዳ ሰዎች መል​ሰው፥ “በን​ጉሡ ዘንድ ለእኛ ዐሥር ክፍል አለን፤ ከእ​ና​ን​ተም እኛ እን​ቀ​ድ​ማ​ለን፤ እኛም በኵር ነን፤ ለዳ​ዊ​ትም ከእ​ና​ንተ እኛ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ ስለ​ምን ናቃ​ች​ሁን? ንጉ​ሡ​ንስ እን​መ​ል​ሰው ዘንድ ከእ​ና​ንተ የእኛ ቃል አይ​ቀ​ድ​ም​ምን?” አሏ​ቸው። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ቃል ከእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ቃል ይልቅ ጠነ​ከረ።


የይ​ሁ​ዳም ሰዎች መጥ​ተው በይ​ሁዳ ቤት ይነ​ግሥ ዘንድ ዳዊ​ትን በዚያ ቀቡት። ሳኦ​ልን የቀ​በ​ሩት የኢ​ያ​ቢስ ገለ​ዓድ ሰዎች ናቸው ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገድ ሁሉ ወደ ኬብ​ሮን ወደ ዳዊት መጥ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “እኛ የአ​ጥ​ን​ትህ ፍላጭ የሥ​ጋህ ቍራጭ ነን።


የኤ​ፍ​ሬም ሰዎ​ችም፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምድ​ያ​ምን ለመ​ዋ​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ ለምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም?” አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣ​ሉት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች