Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 9:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ብላ​ቴ​ኖ​ቹም በሰ​ረ​ገ​ላው ጭነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በመ​ቃ​ብሩ ቀበ​ሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 አገልጋዮቹም በሠረገላ አድርገው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋራ በመቃብሩ ቀበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ቀበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ባሪያዎቹም በሠረገላው ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዳዊትም ከተማ በመቃብሩ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 9:28
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም የኢ​ያ​ሙ​ሃት ልጅ ኢያ​ዜ​ክ​ርና የሳ​ሜር ልጅ ኢያ​ዛ​ብድ መቱት፤ ሞተም፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሜ​ስ​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህ​ናት ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ ገደ​ላ​ቸው፥ የሰ​ዎ​ቹ​ንም አጥ​ንት በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎቹ ላይ አቃ​ጠለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሰ።


አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም በድ​ኑን በሰ​ረ​ገ​ላው አድ​ር​ገው ከመ​ጊዶ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጡት፤ በመ​ቃ​ብ​ሩም ቀበ​ሩት። የሀ​ገ​ሩም ሰዎች የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ዮአ​ክ​ስን ወሰ​ዱት። ቀብ​ተ​ውም በአ​ባቱ ፋንታ አነ​ገ​ሡት።


ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።


በፈ​ረ​ስም ጭነው አመ​ጡት፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ቀበ​ሩት።


ብላ​ቴ​ኖ​ቹም ከሰ​ረ​ገ​ላው አው​ር​ደው ለእ​ርሱ በነ​በ​ረው በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰረ​ገላ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጡት፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አመ​ጡት፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም መቃ​ብር ተቀ​በረ፤ ይሁ​ዳና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሁሉ ለኢ​ዮ​ስ​ያስ አለ​ቀሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች