Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 9:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ኢዩም በእጁ ቀስ​ቱን ለጠጠ፤ ኢዮ​ራ​ም​ንም በጫ​ን​ቃው መካ​ከል ወጋው ፤ ፍላ​ጻ​ውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ውስጥ በጕ​ል​በቱ ላይ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም ኢዩ ቀስቱን በማስፈንጠር ኢዮራምን በትከሻና ትከሻው መካከል ወጋው፤ ፍላጻውም ዘልቆ ልቡን ስለ ወጋው፣ ሠረገላው ውስጥ ዘፍ ብሎ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ኢዩ ቀስቱን ስቦ ባለው ኃይል በመጠቀም ፍላጻውን ባስፈነጠረ ጊዜ ኢዮራምን ወግቶ በትከሻዎቹ መካከል እስከ ልቡ ዘለቀ፤ ኢዮራምም ሞቶ በሠረገላው ውስጥ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ኢዩ ቀስቱን ስቦ ባለው ኀይል በመጠቀም ፍላጻውን ባስፈነጠረ ጊዜ ኢዮራምን ወግቶ በትከሻዎቹ መካከል እስከ ልቡ ዘለቀ፤ ኢዮራምም ሞቶ በሠረገላው ውስጥ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ኢዩም በእጁ ቀስቱን ለጠጠ፤ ኢዮራምንም በጫንቃው መካከል ወጋው፤ ፍላጻውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሠረገላውም ውስጥ ወደቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 9:24
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​ዛ​ሄ​ልም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኢዩ ይገ​ድ​ለ​ዋል፤ ከኢ​ዩም ሰይፍ የሚ​ያ​መ​ል​ጠ​ውን ሁሉ ኤል​ሳዕ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።


አንድ ሰውም ቀስ​ቱን ድን​ገት ገትሮ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ በሳ​ን​ባ​ውና በደ​ረቱ መካ​ከል ወጋው፤ ሰረ​ገ​ለ​ኛ​ው​ንም፥ “መል​ሰህ ንዳ፤ ተወ​ግ​ቻ​ለ​ሁና ከሰ​ልፍ ውስጥ አው​ጣኝ” አለው።


በዚ​ያም ቀን ሰልፍ በረታ፤ ንጉ​ሡም ከጥ​ዋት እስከ ማታ በሶ​ር​ያ​ው​ያን ፊት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተደ​ግፎ ነበር፤ የቍ​ስ​ሉም ደም በሰ​ረ​ገ​ላው ውስጥ ፈሰሰ፤ ማታም ሞተ።


እነ​ር​ሱም እጅግ ፈር​ተው፥ “እነሆ፥ ሁለቱ ነገ​ሥ​ታት በፊቱ ይቆሙ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ እኛስ እን​ዴት በፊቱ መቆም እን​ች​ላ​ለን?” አሉ።


በነ​ጋ​ውም ንጉሡ ወጥቶ ቆመ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ፥ “እና​ንተ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ እነሆ፥ የጌ​ታ​ዬን ቤት የወ​ነ​ጀ​ልሁ የገ​ደ​ል​ኋ​ቸ​ውም እኔ ነኝ፤ እነ​ዚ​ህ​ንስ ሁሉ የገ​ደለ ማን ነው?


ጥበብና ብርታት፥ ምክርም፥ በኃጥእ ዘንድ የሉም።


ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።


ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ከቶም አያመልጡም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች