Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እር​ሱም ግያ​ዝን፥ “እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግ​ላት?” አለው። ሎሌው ግያ​ዝም፤ “ልጅ የላ​ትም፥ ባል​ዋም ሸም​ግ​ሎ​አል” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኤልሳዕም፣ “ታዲያ ምን ይደረግላት” ሲል ጠየቀ። ግያዝም፣ “ልጅ እኮ የላትም፤ ባሏም ሸምግሏል” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባሏም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ኤልሳዕም ግያዝም “ታዲያ ምን ላደርግላት እችላለሁ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “እነሆ፥ ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሽማግሌ ነው” ሲል መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርሱም “እንግዲህ ምን እናድርግላት?” አለ። ግያዝም “ልጅ የላትም፤ ባልዋም ሸምግሎአል፤” ብሎ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 4:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ር​ሃ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ ሳቀም፤ በል​ቡም እን​ዲህ ብሎ አሰበ፥ “የመቶ ዓመት ሰው ስሆን በውኑ እኔ ልጅ እወ​ል​ዳ​ለ​ሁን? ዘጠና ዓመት የሆ​ና​ትም ሣራ ትወ​ል​ዳ​ለ​ችን?”


ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


ራሔ​ልም ለያ​ዕ​ቆብ ልጅ እን​ዳ​ል​ወ​ለ​ደች በአ​የች ጊዜ በእ​ኅቷ ላይ ቀና​ች​ባት፤ ያዕ​ቆ​ብ​ንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአ​ል​ሆነ እሞ​ታ​ለሁ” አለ​ችው።


እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ክብር አከ​በ​ር​ሽኝ ምን ላድ​ር​ግ​ልሽ? ለን​ጉሥ ወይስ ለሠ​ራ​ዊት አለቃ የም​ነ​ግ​ር​ልሽ ጉዳይ እን​ዳ​ለሽ በላት” አለው፤ እር​ስ​ዋም፥ “እኔ በወ​ገኔ መካ​ከል እኖ​ራ​ለሁ” ብላ መለ​ሰች።


እር​ሱም፥ “ጥራት” አለው። ጠራ​ትም በደ​ጃ​ፉም ቆመች።


ልጅም አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም፤ ኤል​ሳ​ቤጥ መካን ነበ​ረ​ችና፤ ሁለ​ቱም አር​ጅ​ተው ነበር፤ ዘመ​ና​ቸ​ውም አልፎ ነበር።


ከዳን ወገን የሆነ ማኑሄ የሚ​ባል አንድ የሶ​ራሕ ሰው ነበረ፤ ሚስ​ቱም መካን ነበ​ረች፤ ልጅም አል​ወ​ለ​ደ​ችም ነበር።


ሁለ​ትም ሚስ​ቶች ነበ​ሩት፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ሐና፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍ​ና​ናም ልጆች ነበ​ሩ​አት፤ ለሐና ግን ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​አ​ትም።


ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች