Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 25:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዓም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹ​ንም ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም ዕቃ​ዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ ብሎ ከናስ ያሠራቸው ሁለት ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፤ ተንቀሳቃሽ የዕቃ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ታላቁን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፥ በክብደታቸው ምክንያት ሊመዝኑአቸው አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ ያሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች፥ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎችና ታላቁን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ፥ በክብደታቸው ምክንያት ሊመዝኑአቸው አልቻሉም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሰሎሞንም ለእግዚአብሄር ቤት የሠራቸውን ሁለቱን ዐምዶች አንዱንም ኵሬ መቀመጫዎቹንም ወሰደ፤ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 25:16
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐሥ​ርም የናስ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ችን ሠራ፤ የአ​ን​ዱም መቀ​መጫ ርዝ​መት አራት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሦስት ክንድ ነበረ።


ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።


የአ​በ​ዛ​ዎች አለ​ቃም ጥና​ዎ​ቹን ከወ​ር​ቅና ከብር የተ​ሠሩ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም ወሰደ።


ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች