Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 21:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የአ​ባ​ቶ​ቹ​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተወ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ገድ አል​ሄ​ደም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ተወ፤ በእግዚአብሔርም መንገድ አልሄደም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የቀድሞ አባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርንም ተወ፤ ለእግዚአብሔርም ቃል ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የቀድሞ አባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርንም ተወ፤ ለእግዚአብሔርም ቃል ለመታዘዝን ፈቃደኛ አልሆነም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የአባቶቹንም አምላክ እግዚአብሔርን ተወ፤ በእግዚአብሔርም መንገድ አልሄደም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 21:22
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ትቶ​ኛ​ልና፥ ለሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ንም ርኵ​ሰት ለአ​ስ​ጠ​ራ​ጢስ፥ ለሞ​አ​ብም አም​ላክ ለኮ​ሞስ፥ ለአ​ሞ​ንም ልጆች አም​ላክ ለሞ​ሎክ ሰግ​ዶ​አ​ልና፥ አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ በፊቴ ቅን ነገ​ርን ያደ​ርግ ዘንድ በመ​ን​ገ​ዶቼ አል​ሄ​ደ​ምና።


አባ​ቱም በሄ​ደ​በት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ አባ​ቱም ያመ​ለ​ካ​ቸ​ውን ጣዖ​ታት አመ​ለከ፥ ሰገ​ደ​ላ​ቸ​ውም።


በእ​ጃ​ችሁ ሥራ ሁሉ ታስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ትታ​ች​ሁ​ኛ​ልና፥ ለሌ​ሎች አማ​ል​ክ​ትም ዐጥ​ና​ች​ኋ​ልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነ​ድ​ዳል፥ አይ​ጠ​ፋ​ምም።


“አን​ተም ልጄ ሰሎ​ሞን ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብን ሁሉ ይመ​ረ​ም​ራ​ልና፥ የነ​ፍ​ስ​ንም አሳብ ሁሉ ያው​ቃ​ልና የአ​ባ​ቶ​ች​ህን አም​ላክ ዕወቅ፤ በፍ​ጹም ልብና በነ​ፍ​ስህ ፈቃ​ድም ተገ​ዛ​ለት፤ ብት​ፈ​ል​ገው ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ብት​ተ​ወው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይተ​ው​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድ​ርም አድ​ምጪ፤ ልጆ​ችን ወለ​ድሁ፤ አሳ​ደ​ግ​ሁም፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፁ​ብኝ።


ኀጢ​አ​ተኛ ወገ​ንና ዐመፅ የተ​ሞ​ላ​በት ሕዝብ፥ የክ​ፉ​ዎች ዘር፥ በደ​ለ​ኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮ​ላ​ችሁ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተዋ​ች​ሁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ቅዱስ አስ​ቈ​ጣ​ች​ሁት።


ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገ​ሮ​ችን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የሕ​ይ​ወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተ​ው​ኛል፥ የተ​ነ​ደ​ሉ​ትን ውኃ​ው​ንም ይይዙ ዘንድ የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ጕድ​ጓ​ዶች ለራ​ሳ​ቸው ቈፍ​ረ​ዋል።


ነፍሴ በዛ​ለ​ች​ብኝ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሰ​ብ​ሁት፤ ጸሎ​ቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅ​ደ​ስህ ትግባ።


ያዕ​ቆብ በላ፤ ጠገ​በም፤ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን ጥጋብ አቀ​ና​ጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈ​ጠ​ረ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ተወ፤ ከሕ​ይ​ወቱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ራቀ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች