Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 18:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ራፋ​ስ​ቂስ ግን፥ “በውኑ ጌታዬ ይህን ቃል እና​ገር ዘንድ ወደ እና​ን​ተና ወደ ጌታ​ችሁ ልኮ​ኛ​ልን? ከእ​ና​ንተ ጋር ኵሳ​ቸ​ውን ይበሉ ዘንድ ሽን​ታ​ቸ​ው​ንም ይጠጡ ዘንድ በቅ​ጥር ላይ ወደ ተቀ​መ​ጡት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ምን?” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ነገር ግን የጦር አዛዡ መልሶ፣ “ጌታዬ እነዚህን ቃሎች እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነበርን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኵስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎችም አይደለምን?” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱም “የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት የሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆኑ፥ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት ነው” ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱም “የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣችሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? ከቶ አይደለም፤ ልክ እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት የሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆኑ፥ እኔ የምናገረውን በቅጽሩ ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት ነው” ሲል መለሰላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ራፋስቂስ ግን “ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 18:27
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ተር​ታ​ን​ንና ራፌ​ስን ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላካ​ቸው። ወጥ​ተ​ውም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ፤ በአ​ጣ​ቢ​ውም እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ዪ​ኛ​ዪቱ ኩሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆሙ።


የኬ​ል​ቅ​ዩም ልጅ ኤል​ያ​ቄም ሳም​ና​ስም ዮአ​ስም ራፋ​ስ​ቂ​ስን፥ “እኛ እን​ሰ​ማ​ለ​ንና በሱ​ር​ስት ቋንቋ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ተና​ገር፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ቋንቋ አት​ና​ገ​ረን፤ በቅ​ጥ​ርም ላይ ያለው ሕዝብ በሚ​ሰ​ማው ቋንቋ ለምን ትና​ገ​ራ​ለህ?” አሉት።


ራፋ​ስ​ቂ​ስም ቆሞ በታ​ላቅ ድምፅ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ እን​ዲህ ብሎ ጮኸ፥ “የታ​ላ​ቁን የአ​ሦር ንጉሥ ቃል ስሙ፤


በሰ​ማ​ር​ያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነ​ሆም፥ የአ​ህያ ራስ በኀ​ምሳ ብር፥ የድ​ርጎ አንድ አራ​ተኛ የሚ​ሆን ኵስሐ ርግ​ብም በአ​ም​ስት ብር እስ​ኪ​ሽጥ ድረስ ከበ​ቡ​አት።


አንድ ሆነው በል​ባ​ቸው በየ​ሕ​ዝ​ባ​ቸው አሉ፦ “ኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በዓ​ላት ከም​ድር እን​ሻር


ራፋ​ስ​ቂስ ግን፥ “ጌታዬ ይህን ቃል እና​ገር ዘንድ ወደ እና​ን​ተና ወደ ጌታ​ችሁ ልኮ​ኛ​ልን? ከእ​ና​ንተ ጋር ኵሳ​ቸ​ውን ይበሉ ዘንድ፥ ሽን​ታ​ቸ​ው​ንም ይጠጡ ዘንድ በቅ​ጥር ላይ ለተ​ቀ​መ​ጡት ሰዎች እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን?” አላ​ቸው።


ዳሌጥ። ጡት የሚ​ጠ​ባው የሕ​ፃን ምላስ ከጥም የተ​ነሣ ወደ ትና​ጋው ተጣ​በቀ፤ ሕፃ​ናት እን​ጀራ ለመኑ፤ የሚ​ቈ​ር​ስ​ላ​ቸ​ውም የለም።


ሄ። የጣ​ፈጠ ነገር ይበሉ የነ​በሩ በመ​ን​ገድ ጠፉ፤ በቀይ ግምጃ ያድጉ የነ​በሩ የፍግ ክምር አቀፉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ር​ሱን በም​በ​ት​ን​ባ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ንጹሕ ያል​ሆነ እን​ጀ​ራ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ” አለ።


እር​ሱም፥ “እነሆ በሰው ኵስ ፋንታ የከ​ብት ኩበት ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ጀ​ራ​ህን ትጋ​ግ​ራ​ለህ” አለኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች