Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ራፋ​ስ​ቂ​ስም አላ​ቸው፥ “ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ታላቁ ንጉሥ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ይህ የም​ት​ተ​ማ​መ​ን​በት መተ​ማ​መኛ ምን​ድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የጦር አዛዡም እንዲህ አላቸው፤ “ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፤ “ ‘ታላቁ ንጉሥ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ እስከዚህ የተማመንህበት ነገር ምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከአሦር የጦር አዛዦች አንዱ እንዲህ አላቸው፦ “ለሕዝቅያስ እንዲህ በሉት ‘ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ለመሆኑ እንደዚህ አድርገህ የተማመንክበት ነገር ምንድነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ከአሦር የጦር አዛዦች አንዱ እንዲህ አላቸው፦ “ለሕዝቅያስ እንዲህ በሉት ‘ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ለመሆኑ እንደዚህ አድርገህ የተማመንክበት ነገር ምንድን ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ራፋስቂስም አላቸው “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት ‘ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ ይህ የምትታመንበት መተማመኛ ምንድር ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 18:19
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ተር​ታ​ን​ንና ራፌ​ስን ራፋ​ስ​ቂ​ስ​ንም ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላካ​ቸው። ወጥ​ተ​ውም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ደረሱ፤ በአ​ጣ​ቢ​ውም እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ዪ​ኛ​ዪቱ ኩሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆሙ።


እና​ን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብት​ሉኝ፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመነ፤ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ከይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ እር​ሱን የሚ​መ​ስል አል​ነ​በ​ረም።


“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።


እና​ንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ልባ​ች​ሁን ታከ​ብ​ዳ​ላ​ችሁ? ከንቱ ነገ​ርን ለምን ትወ​ድ​ዳ​ላ​ችሁ? ሐሰ​ት​ንም ለምን ትሻ​ላ​ችሁ?


ራፋ​ስ​ቂ​ስም አላ​ቸው፥ “ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ታላቁ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በማን ትተ​ማ​መ​ና​ለህ?


እነሆ፥ በዚያ በተ​ቀ​ጠ​ቀጠ በሸ​ን​በቆ በትር በግ​ብፅ ትታ​መ​ና​ለህ፤ ሰው ቢመ​ረ​ኰ​ዘው ተሰ​ብሮ በእጁ ይገ​ባል፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ፈር​ዖን ለሚ​ታ​መ​ኑ​በት ሁሉ እን​ዲሁ ነው።


አን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብትል፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በዚህ መሥ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?


“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።


የሔ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ፥ የሴ​ፈ​ር​ዋይ ከተማ፥ የሄ​ናና የዒዋ ነገ​ሥ​ታት ወዴት አሉ?”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች