Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 14:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በጋትሔፌር ነቢይ፣ በአማቴ ልጅ በባሪያው በዮናስ አማካይነት እንደ ተናገረው፣ ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ እስከ ሙት ባሕር ድረስ የነበረውን የእስራኤልን ድንበር አስመለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የጋትሔፌር በነበረው በአማቴ ልጅ በባሪያው በነቢዩ በዮናስ እንደ ተናገረው እንደ እስራኤል አምላክ እንደ እግዚአብሔር ቃል የእስራኤልን ድንበር ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 14:25
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።


በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።


በዚ​ያም ወራት እዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ራ​ኤ​ልን ያጠፋ ጀመረ፤ አዛ​ሄ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል ዳርቻ ሁሉ መታ​ቸው።


አዛ​ሄ​ልም ከአ​ባቱ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ እጅ በሰ​ልፍ የወ​ሰ​ዳ​ቸ​ውን ከተ​ሞች የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ መልሶ ከአ​ዛ​ሄል ልጅ ከወ​ልደ አዴር እጅ ወሰደ። ዮአ​ስም ሦስት ጊዜ መታው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ከተ​ሞች መለሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል ታዳ​ጊን ሰጠ፤ ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም እጅ ዳኑ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ ቀድ​ሞው ጊዜ በድ​ን​ኳ​ና​ቸው ተቀ​መጡ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ሁሉ አል​ራ​ቀም።


በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ እነሆ እኔ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ሁን ሕዝብ አስ​ነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ከሐ​ማት መግ​ቢያ ጀም​ረው እስከ ዐረባ ወንዝ ድረስ ትገቡ ዘንድ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ች​ሁም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።


ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።” ትቶአቸውም ሄደ።


ከመ​ካ​ናራ ወሰን ከፈ​ስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥ​ራቅ እስከ ዓረባ ባሕር እር​ሱም የጨው ባሕር ድረስ ዓረ​ባን፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው።


ከዚ​ያም ወደ ጌቤሮ ምሥ​ራቅ ወደ ከታ​ሤም ከተማ ያል​ፋል፤ ወደ ሪና​ሞን ወደ ማታ​ር​ዮዛ ይወ​ጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች