Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዮአ​ስም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም በዙ​ፋኑ ላይ ተቀ​መጠ፤ ዮአ​ስም በሰ​ማ​ርያ ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ጋር ተቀ​በረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ዮአስም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓም በእግሩ ተተክቶ በዙፋኑ ተቀመጠ። ዮአስም በሰማርያ ከእስራኤል ነገሥታት ጋራ ተቀበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ከዚህ በኋላ ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያም በሚገኘው መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከዚህ በኋላ ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያም በሚገኘው መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዮአስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ኢዮርብዓምም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ዮአስም በሰማርያ ከእስራኤል ነገሥታት ጋር ተቀበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 13:13
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


ይህ ባይ​ሆን፥ ጌታዬ ንጉሥ ከአ​ባ​ቶ​ችህ ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ እኔና ልጄ ሰሎ​ሞን እንደ ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ቈ​ጠ​ራ​ለን።”


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አለው፥ “ዐሥር ቅዳጅ ውሰድ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን እጅ መን​ግ​ሥ​ቱን እለ​ያ​ታ​ለሁ፤ ዐሥ​ሩ​ንም ነገ​ዶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ዳዊ​ትም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ተቀ​በረ።


የቀ​ረ​ውም የዮ​አስ ነገር፥ ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር የተ​ዋ​ጋ​በት ኀይሉ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ።


ኢዮ​አ​ካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፥ ልጁም ዮአስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


የቀ​ረ​ውም ያደ​ረ​ገው የዮ​አስ ነገር፥ ኀይ​ሉም፥ ከይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ከአ​ሜ​ስ​ያስ ጋር እንደ ተዋጋ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በአ​ሜ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዮ​አስ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመ​ትም ነገሠ።


ለኢዩ፥ “ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” ተብሎ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።


በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት በዖ​ዝ​ያ​ንና በኢ​ዮ​አ​ታም በአ​ካ​ዝና በሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም ዘመን በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች