Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ዘመን፣ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ ከተማ በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ ዐሥራ ስድስት ዓመትም ገዛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ በነገሠ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ በነገሠ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በእስራኤል ላይ በሰማርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ስድስትም ዓመት ነገሠ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 13:10
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ በል​ቤም ያለ​ውን ሁሉ በአ​ክ​አብ ቤት ላይ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” አለው።


ኢዩ በነ​ገሠ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት ኢዮ​አስ ነገሠ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ሳቢያ የተ​ባ​ለች የቤ​ር​ሳ​ቤህ ሴት ነበ​ረች።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ካ​ዝ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አስ በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮ​አ​ካዝ በሰ​ማ​ርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመ​ትም ነገሠ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄደ።


ኢዮ​አ​ካ​ዝም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት፥ ልጁም ዮአስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


በእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ በኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ በዮ​አስ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ነገሠ።


የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​አስ ልጅ አሜ​ስ​ያስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ከዮ​አስ ሞት በኋላ ዐሥራ አም​ስት ዓመት ኖረ።


ለኢዩ፥ “ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” ተብሎ የተ​ነ​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እን​ዲ​ሁም ሆነ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች