Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዩን፥ “በፊቴ ቅን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና፥ በል​ቤም ያለ​ውን ሁሉ በአ​ክ​አብ ቤት ላይ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ልጆ​ችህ እስከ አራት ትው​ልድ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን ላይ ይቀ​መ​ጣሉ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 እግዚአብሔርም ኢዩን፣ “በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር ስላደረግህና በአክዓብም ቤት ላይ እንዲደርስ በልቤ ያለውን ሁሉ ስለ ፈጸምህ፣ ዘርህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ኢዩን “በአክዓብ ተወላጆች ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን ባዘዝኩህ መሠረት ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እሰጥሃለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ኢዩን “በአክዓብ ተወላጆች ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን ባዘዝኩህ መሠረት ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እሰጥሃለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እግዚአብሔርም ኢዩን “በፊቴ ቅን ነገር አድርገሃልና፥ በልቤም ያለውን ሁሉ በአክዓብ ቤት ላይ አድርገሃልና፥ ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 10:30
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንድ ነቢ​ይም ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚ​መ​ጣው ዓመት ይመ​ጣ​ብ​ሃ​ልና፥ በርታ፤ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ዕወቅ” አለው።


እነ​ዚ​ህም በእ​ነ​ዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ተጋ​ጠሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሶ​ር​ያ​ው​ያን በአ​ንድ ቀን መቶ ሺህ እግ​ረኛ ገደሉ።


ኢዩም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በሰ​ማ​ር​ያም ቀበ​ሩት። በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ ኢዩ​አ​ካዝ ነገሠ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ካ​ዝ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አስ በሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮ​አ​ካዝ በሰ​ማ​ርያ ነገሠ፤ ዐሥራ ሰባት ዓመ​ትም ነገሠ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ በሠ​ላሳ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት የኢ​ዮ​አ​ካዝ ልጅ ዮአስ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በሰ​ማ​ርያ ዐሥራ ስድ​ስት ዓመት ነገሠ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​አስ ልጅ በአ​ሜ​ስ​ያስ በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዮ​አስ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም በሰ​ማ​ርያ መን​ገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመ​ትም ነገሠ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እንደ አባ​ቶቹ እንደ እስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት አን​ቀ​ላፋ፤ ልጁም ዘካ​ር​ያስ በፋ​ን​ታው ነገሠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ከጥ​ቂት ዘመን በኋላ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ልን ደም በይ​ሁዳ ቤት ላይ እበ​ቀ​ላ​ለ​ሁና፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መን​ግ​ሥ​ትን እሽ​ራ​ለ​ሁና ስሙን ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ብለህ ጥራው፤


የቃል ኪዳ​ኔ​ንም በቀል ይበ​ቀ​ል​ባ​ችሁ ዘንድ ሰይፍ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ ከተ​ማ​ች​ሁም ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ፤ ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እጅ ተላ​ል​ፋ​ችሁ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች