Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ኤል​ያ​ስም፥ “እኔስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰ​ማይ ትው​ረድ፤ አን​ተ​ንም፥ አም​ሳ​ው​ንም ሰዎ​ች​ህን ትብላ” አለው። እሳ​ትም ከሰ​ማይ ወርዳ እር​ሱ​ንና አም​ሳ​ውን ሰዎች በላች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኤልያስም መልሶ፣ “እኔ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንሁ እሳት ከሰማይ ወርዳ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ትብላ!” አለው፤ ከዚያም እሳት ከሰማይ ወርዳ እርሱንና ሰዎቹን ፈጽማ በላች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር እሳት መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር እሳት መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ፤” አለው። የእግዚአብሔርም እሳት ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳ ሰዎቹን በላች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 1:12
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።


ደግ​ሞም ሌላ የአ​ምሳ አለቃ ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ላከ​በት፤ የአ​ምሳ አለ​ቃ​ውም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ፦ ና፤ ፈጥ​ነህ ውረድ ይላል” ብሎ ተና​ገረ።


ንጉ​ሡም ደግሞ ሦስ​ተኛ የአ​ምሳ አለቃ ከአ​ምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ ሦስ​ተ​ኛ​ውም የአ​ምሳ አለቃ ወጥቶ በኤ​ል​ያስ ፊት በጕ​ል​በቱ ተን​በ​ረ​ከ​ከና ለመ​ነው እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሆይ! ሰው​ነ​ቴና የእ​ነ​ዚህ የአ​ም​ሳው ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ሰው​ነት በፊ​ትህ የከ​በ​ረች ትሁን።


እር​ሱም ገና ይህን ሲና​ገር ሌላ መል​እ​ክ​ተኛ መጥቶ፦ ለኢ​ዮብ እን​ዲህ አለው፥ “እሳት ከሰ​ማይ ወደ​ቀች፥ በጎ​ች​ህ​ንም አቃ​ጠ​ለች፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ህ​ንም በላች፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቶ በላ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሞቱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች